Accessibility Settings

color options

monochrome muted color dark

reading tools

isolation ruler

ሪፖርት ማድረግ

በአፍሪካ በኮቪድ 19 ዙሪያ የምርመራ ዘገባ ለመሥራት ጠቃሚ ነጥቦች

Read this article in

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ በኮቪድ 19 ዙሪያ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በሚመለከት ለኅብረቱ ንግግር ሲያደርጉ፤

በአፍሪካ የምርመራ ዘገባ ጋዜጠኞች በአኅጉሪቱ እየጨመረ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በማጋለጥና መንግሥትን ተጠያቂ በማድረግ ወሳኝ ሚና አየተጫወቱ ነው።

የምርመራ ዘገባዎች አንዳንድ መንግሥታትን ለኮቪድ 19 ዝግጁ ነን ከሚል መታበይ ነቅለው አውጥተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይፋ የሆኑትም አሻሚ በሆኑ የሕክምና አሰጣጦችና በአጭበርባሪዎች አለአግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ የሕዝብ ሀብትን ከብክነት ለመከላከል አስችለዋል።

አሁን ላይ ታድያ እየታየ ያለው ከፍተኛ የስርጭት መጠን፣ ከዓለም ጤና ድርጅት የሚወጡ አስፈሪ የሞት ትንበያዎች እንዲሁም እየባሰ የመጣው ሥራ አጥነት ተዳምሮ በአኅጉሪቱ በሚገኙ አገራት ቫይረሱ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽእኖ አሳሳቢ አድርጎታል። በግንቦት ወርም የዓለም ጤና ድርጅት አስደንጋጭ አዙሪት እንደሚኖርና፣ በዚህም ቫይረሱ የምግብ ዋስትና ላይ ተጽእኖ ሲያሳድር፣ የምግብ እጥረት የሰዎችን የመከላከል አቅም ያሳንሳል ሲል አሳስቧል። ይህም ቫይረሱን የበለጠ ገዳይ ያደርገዋል ብሎ ነበር። በተጨማሪም አሳሳቢ የሆነው በአፍሪካ ያለው የሕክምና ቁሳቁስ ግብዓት አለመኖርና በአኅጉሪቱ የተንሰራፋው ድህነት ነው።

በአፍሪካ ካው የምርመራ ጋዜጠኝነት ድርሻ ከፍታ ጋር በተገናኘ፣ አራት ፓናሊስቶች ቫይረሱ ለአፍሪካ ስጋት ነው በሚል በቫይረሱ ዙሪያ የሚሠሩ ዘገባዎችን ማድረግ ስለሚቻልበት ሥልት ተነጋግረዋል። ይህም ባለፈው ሳምንት በGIJN ዌብናር የተካሄደና ከ57 አገራት የተውጣጡ 260 ጋዜጠኞች ያሳተፈ ነው።

ከውይይቱ የተገኘው ዋና መልዕክት ግልጽ ነበር። ይህም ዘገባችሁን በለመዳችሁት ቅኝት ጀምሩ፣ ምርመራችሁን ቀለል አድርጉት፣ ከሥራ ባልደረቦቻችሁ ጋር ተባበሩ፣ ሳይንቲስቶች ምርኩዝ አድርጉ እና ምንም እንኳ ዘገባው ደረቅ ያለ ሳይንሳዊ ጉዳይ ወይም የመረጃ ዘገባ ቢሆን እንኳ፣ ሰዎች ላይ አተኩሩ የሚሉ ናቸው።

ዳዮ አይታን፣ በናይጄሪያ የዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) ዋና ሥራ አስኪያጅ በንግግሩ፣ ካቢኔው ‹ናይጄሪያ ለወረርሽኙ ዝግጁ ናት› ብሎ መጀመሪያ ሰሞን ሲያሰማ የነበረውን ሙግት ካጣጣለ በኋላ፣ በአገሩ (በናይጄሪያ) ያሉ ጋዜጠኞች መንግሥት ምላሽ እንዲሰጥ በመቀስቀስና በማንቀሳቀስ በኩል ቀጥተኛ ተጽእኖ ነበራቸው ይላል።

‹‹ሁኔታው የተሻሻለው በተሰጠው ሽፋን ምክንያት ነው›› አለ፤ በተጨማሪም ይህን ጠቀሰ፣ ‹‹በመንግሥት ኮምዩኒኬሽን በኩል፣ ነገሮች እንደ ወትሮው እንዳልሆኑና እንደማይሆኑ ከጋዜጠኞች የታየ ምልክት ነበር።››

በሚያዝያ ወር የመጀመሪያ ሳምንት፣ ዓለማቀፉ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) በናይጄሪያ በኮሮና ቫይረስ ላይ እየሠሩ ያሉ የጤና ባለሞያዎች የተመደበውን ትንሹን ክፍያ፣ ማለትም በወር 13.64 የአሜሪካን ዶላር ሌሎች አገራት ከሚያደርጉት ክፍያ ጋር አነጻጽሮ ነበር። በንጽጽር የቀረቡትም በ2015 ኢቦላ ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ በሴራሊዮንና ላይቤሪያ ለጤና ባለሞያዎች ይከፈል የነበረው በድምሩ 460 እና 825 ዶላር ነው። በተጨማሪም የምርመራ ዘገባ ቡድኑ፣ በጋና ለጤና ባለሞያዎች የሚከፈለውን የመድኅን (ኢንሹራንስ) ሽፋን በማጤን፣ ለተመሳሳይ ቀውስ ጊዜ ከሚከፈለው (361 ዶላር) የመድኅን ሽፋን ጋር አንጻጽሮታል።

ይህም ዘገባ ይፋ ከሆነ ከኹለት ሳምንት በኋላ፣ ለአንዳንድ ናይጄሪያዊያን ሐኪሞች የአደጋ ጊዜ ክፍያውን አምስት እጥፍ አሳድጎታል። እናም ይህን ያነሳው አይታን፣ ቀላልና አጽንኦት በሚሰጥ መንገድ የሚደረግ አዘጋገብ በወረርሽኙ የመጀመሪያ ሰሞን ውጤታማ እንደነበር አስረድቷል።

በስምንተኛውና በኢንግሊዘኛ ቋንቋ በተካሄደውና በወረርሽኙ ዙሪያ ምርምር ስለማድረግ ዓለማቀፉ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) በዌብናር ባዘጋጀው ተከታታይ ውይይት፣ በመጨረሻ የተደረሰበት ሁሉን የሚያስማማ ዕይታ አለ። ይህም ባለፉት ኹለት ወራት የአፍሪካ ጋዜጠኞችና ዘጋቢዎች ለመንግሥት ምላሽ ግብረ መልስ በመስጠት ጥሩ ሥራ መሥራታቸው ነው፤ በተለይ ሐሰተኛ መግለጫዎችን በማጋለጥ። ያም ሆኖ ከየእለቱ አጀንዳ በዘለለ፣ ብዙዎቹ ተጠያቂነትን በሚመለከት ያሉ ችግሮችን ለመለየትና ለማሸነፍ እየታገሉ ይገኛሉ።

በአፍሪካ የሚድያ ልኅቀት ማእከል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፒተር ሚዌሲጌ እንዳለው፣ ግልጽነት እንዲሁም ጥርጣሬ ሲኖርም አለመደበቅ፣ በአፍሪካ ለኮቪድ 19 ጉዳዮች የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ወሳኝ ነበር። ይህም ለሕዝብ ፍላጎት እንዲሁም ትክክለኛ ዘገባ ለመሥራትም ጠቅሟል።

ቀጥሎም ሲናገር እንዲህ አለ፣ ‹‹ይህ አሁንም በሥራ ላይ ያለ ጉዳይ ነው። በቁጥሮች ዙሪያ ጥርጣሬዎች አሉ፣ በዚህ ዙሪያ ባለሞያዎችም አይስማሙም። ስለዚህ እኛም በሥራችን ከምናውቃቸው እውነቶች ጎን ለጎን፣ ለእነዚህ ጥርጣሬዎችም እውቅና እንሰጣለን።››

በሚያዝያ ወር፣ ሚዌሲጌ እና ቡድኑ፣ በአፍሪካ ለሚገኙ ጋዜጠኞች የሚሆኑ የዘገባ አንጻሮችን ዝርዝር ያካተተ የሐሳብ መድብል ለህትመት አብቅተዋል። ይህም የግብርና ምርት አቅርቦት ላይ ካሳደረው ተጽእኖ እስከ ሃይማኖት የሚዘልቅ ነው። እርሱም እንዳለው ታድያ፣ በአንድ በኩል ዝርዝሩ የተዘጋጀው ዘጋቢዎች ሰፊ የሆነውን ወረርሽኝ በመዘገብ በኩል ያላቸውን ዕይታና አቅም እንዲጨምሩ ለማገዝ ሲሆን፣ እንዲሁም ከጤና ዘርፍ ባሻገር ወረርሽኙ ሊኖረው የሚችለውን ቁጥር ስፍር የሌለው ተጽእኖ እንዲመለከቱ ለመርዳት ነው።

ሚውሲጌ በንግግሩ አክሎ እንዲህ አለ፤ ‹‹እንደ መገናኛ ብዙኀን፣ በመላው አፍሪካ የተለያዩ አገራት የሚሰጠውን ምላሽ አኳኋን መረዳት ያስፈልገናል። አንድን ጥያቄም ደጋግመን መጠየቅ አለብን። ገንዘቡን መከተል ያስፈልገናል፣ እውነት ለታለመለት ውሏል ወይ?››

በናይጄሪያ የዳታፋይት መሥራች ጆሹዋ ኦሊፌሚ፣ ለአፍሪካ ዘጋቢዎች በርካታ ምንጮችና ትንታኔ ለመሥራት የሚያስችሉ የመረጃ አውዶች አሉ። እናም ደረቅ በሆኑ ዝርዝር መረጃዎች ላይ ቢያጠነጥኑ እንኳ፣ ትኩረታቸው ሰዎች ላይ ሊሆን ይገባል ብሏል።

ወሳኝ የሆኑና በዲጂታል ሊገኙ የሚችሉ ለምሳሌ እንደወረርሽኝ ሰሞን ኦዲት ያሉ መሠረታዊና አስፈላጊ ሰነዶች እንደሚዘገዩ የታወቀ ነው የሚለው ኦሊፌሚ፣ በአንጻሩ ዘጋቢዎች ብዙ ምንጮች ሊገኙ የሚችሉባቸው ማኅበራዊ ሚድያዎችን መመልከትና ከዛ ውጪ ደግሞ መደበኛ ምንጮችን በመጠቀም የሰነድ እጥረት ክፍተቱን ለመሙላት መጣር ይገባቸዋል ይላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በደቡብ አፍሪካ ብሄክሲሳ የጤና ጋዜጠኝነት ማእከል መሥራችና ዋና አዘጋጅ ሚያ ማላን፣ ጋዜጠኞች የጤና ዘገባዎችን በሚሠሩ ጊዜ ጥቅም ላይ ማዋል የሚችሏቸውን የጤና ጉዳይ አዘጋገብ ጠቃሚ ምክሮችን አጋርታለች። ይህም አንባቢዎች ለወትሮ ቢሆን ለማንበብ ጊዜ የማይሰጡትን የሕክምና ጉዳይ እንዴት ‹በብልጠት› ማስነበብና ማሳየት ይቻላል ለሚለው ጠቃሚ ነጥብን ያካተተ ነው።

ማላን ካጋራቻቸው ጠቃሚ ነጥቦች መካከል አንደኛው፣ አንባቢዎች ወትሮ ቢሆን ገሸሽ የሚያደርጉትን የሕክምና ጉዳይ እንዲያነቡና እንዲመለከቱ የሚረዱ ‹ብልሃቶች› ይገኙበታል፤ (Pullout Malan <tricks>)

ማላን እንዳለችው፣ ጠንካራ የሰዎችን ገጽ መሳል የቻሉና ያንን ያስቀደሙ ትረካዎችና የሳይንስ ዘገባዎች አንባቢ አድማጭ ወይም ተመልካችን ለመሳብ የተሻለ አቅም አላቸው። እናም ማእከሉ ሰዎች በጽሑፍ ቢሆን ጨርሶ ለንበብ የማይመርጡትን ጉዳይ፣ በቪድያ በመጠቀም እንዲመለከቱ ማድረጉን ተናግራለች።

የተለያዩ ዘገባዎችንና መረጃዎችን በማጠናቀር በትረካ መልክ የሚያዘጋጀው ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ የሚድያ ተቋም የሆነው ብሄክሲሳ፣ የተለያዩ ተጽእኖ መፍጠር የቻሉ ዘገባዎችን አቅርቧል። ከእነዚህም መካከል ያልተረጋገጡ ነገር ግን ለወረርሽኙ መድኃኒት ናቸው ተብሎ የተነገረላቸው እንደ ማዳጋስካሩ መድኃኒት ምርመራ መዘግየትን እንዲሁም የደቡብ አፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነ ምላሽን በሚመለከት ከሳይንቲስቶች ጋር የተደረጉ ቃለምልልሶችን አቅርቧል። እንዲሁም አስደንጋጭና የሕዝብ ገንዘብን በመጠቀም የሌለውን ‹ክትባት› ለመግዛት ያቀደውን የአንድ ትልቅ ከተማ ከንቲባ ጉዳይ ሽፋን ሰጥተዋል።

ኃይል የነበረውና መጀመሪያ የወጣው ዘለግ ያለው ዘገባ፣ የዌብናሩ አስተባባሪ የነበረችውና በኬንያ ሲቲዝን ቲቪ የልዩ ፕሮጀክቶች አዘጋጅ አሻ ምዊሉ የወጣው ዘገባ ሲሆን፣ ምዊሉ እንዳለችው በናይሮቢ ዋና በተባሉ ለይቶ ማቆያዎች ሆና ዘገባዎችን ከሠራች በኋላ ለ14 ቀናት ራሷን ለይታ አቆይታለች።

ከፓናል ውይይቱ የተነሱ አጫጭር ጠቃሚ ነጥቦች፤

  • ከወረርሽኙ ጋር የተገናኘ የምርመራ ዘገባ ይፋ ስታደርጉ፣ በመደበኛ ርዕሰ ጉዳዮችና ምንጮች ጀምሩ፣ ማንኛውም የሕይወት ጉዳይ በቫይረሱ ይነካልና። እንደ ግብርና፣ ሃይማኖት እና ትምህርት የመሳሰሉ ጉዳዮች በአንድ በኩል በቂ ሽፋን ያላገኙ ናቸው፣ አልያም የተጠያቂነት ጉዳይ ሲነሳ በብዛት የሚጠቀሱ አይደሉም።
  • በምርምራችሁ ገንዘቡንና ሳይንሱን ተከተሉ፣ ታሪክ ስትነግሩ ግን ሰዎች ላይ አተኩሩ። በቻላችሁት መጠን ሳይንቲስቶችን፣ ባለድርሻ የሚባሉ አካላትንና የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ለሁሉም የታሪካችሁ አካል ለሆኑ ሰዎች ስም ስጡ።
  • በትክክል እርግጠኛ መሆን ስላልተቻለበት መረጃ፣ ስለማታውቁት ነጥብ እንዲሁም ዘገባው በወጣ ጊዜ መረጃው አልፎበት ሊሆን ይችላል የሚለውን በሚመለከት፣ ለአንባቢና አድማጭ ግልጽ አድርጉ።
  • አደጋን መከላከል ማለት አንድን ዘገባ መስዋዕት አድርጎ ከመናገር መቆጠብ ማለት አይደለም። ጥልቀት ያላቸውና ተራኪ ዘገባዎች በስልክ ወይም በስካይፒ ሊደረጉ ይችላሉ። አንድ የብሄክሲሳ ዘጋቢ፣ ቫይረሱን በሚመለከት የሰዎች ንክኪ የት ተነስቶ የት ደረሰ የሚለውን ለመለየት እንዴት እንደሚሠራ ለማጣራት፣ ከአንድ ቁልፍ ምንጭ ጋር በስልክ ከአምስት ሰዓታት በላይ አሳልፏል።
  • በሳይንሳዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሳይንቲስቶችን ደውሎ የመጠየቅ ልምድ አዳብሩ። ለጤና ጉዳይ መረጃ ለማግኘትም እንደ ‹the Mayo Clinic› ያሉ ታማኝ ድረ ገጾችን ተጠቀሙ። ተዓማኒ ለሆነ የጥናታዊ ጽሑፍ ግብዓት ፍለጋም፣ እንደ‹PubMed.› ያሉ ምንጮችን ጥቅም ላይ አውሉ።
  • አሁን መንግሥት ለኮቪድ 19 የሚሰጠውን ምላሽ ቀድሞ ተከስተው ለነበሩ ወረርሽኞች ከሰጠው ምላሽ ጋር አነጻጽሩ።
  • ለውስጣዊ የፖለቲካ ዓላማ ሲባል ሆነ ብለው የኮቪድ 19 ኬዞችን የሚደብቁ ግዛቶችን፣ ክልል እና ከተሞችን ተከታተሉ። እንዲያም ሆኖ እንደ እናንተው አንዳንድ ዘጋቢዎች በጉዳዮ ላይ ምርመራ በማድረጋቸው ጉዳትና እስራት እንደደረሰባቸው አስታውሱ።
  • ወረርሽኙ ባለፉት ስድስት ወራት ያሳደረውን ተጽእኖና ተመልኩቱና፣ የመንግሥት ባለድርሻዎች በእቅዳቸው ከተጽእኖው ጋር አብረው መራመድ ችለው እንደሆነ ቃኙ።
  • በወረርሽኙ ወቅት መረጃዎች ሊደበቁ ወይም ሊከለከሉ በሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ፣ ከማኅበራዊ ሚድያ በመነሳት እንዲሁም ከዛ ባሻገር ያሉ ሰነዶችን በማገላበጥ አዳዲስ መረጃ ማግኘትን ከግምት ውስጥ አስገቡ።
  • ከሆስፒታል ከወጡና ከቫይረሱ ነጻ ከተባሉ አስቀድሞ በቫይረሱ ተይዘው ከነበሩ ሰዎች ጋር ቃለመጠይቅ አድርጉ። እነዚህ ሰዎች ወደቤታቸው ከተመለሱ በኋላ፣ ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ስለልምዳቸውና ስላሳለፉት ለመናገር ዝግጁና ክፍት ናቸው።
  • ከተመሳሳይ ተቋማት ጋር ይልቁንም ከእናንተ የሙያ አቅምና ኃይል በላይ በሆነ ዘገባ ወይም ከድንበራችሁ አልፎ ባሉ ዘገባዎች ዙሪያ፣ ትብብር አድርጉ።

ሮዋን ፊሊፕ የዓለማቀፉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ ዘጋቢ ነው። አስቀድሞ በደቡብ አፍሪካ የሰንደይ ታይምስ ከፍተኛ ዘጋ ሆኖ አግልግሏል። እንደ ውጪ ወኪል፣ ዜናዎች፣ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሙስና እና ግጭቶችን በበርካታ አገራት ተዘዋውሮ ዘግቧል።

Republish our articles for free, online or in print, under a Creative Commons license.

Republish this article


Material from GIJN’s website is generally available for republication under a Creative Commons Attribution-NonCommercial 4.0 International license. Images usually are published under a different license, so we advise you to use alternatives or contact us regarding permission. Here are our full terms for republication. You must credit the author, link to the original story, and name GIJN as the first publisher. For any queries or to send us a courtesy republication note, write to hello@gijn.org.

Read Next

የናይጄሪያው ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) በኮቪድ 19 ምላሽ ተጠሪነትን ለመፍጠር እያደረገ ያለው ግፊት

መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።