Accessibility Settings

color options

monochrome muted color dark

reading tools

isolation ruler

ጠቃሚ ነጥቦች፣ መሣሪያዎችና ተጨማሪ ሥልጠናዎችን እየፈለጉ ነው? ከታች የሚታዩት መመሪያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ ተጨባጭ ጥናቶችን እና ምሳሌዎችን ያቀርባሉ። አብዛኞቹ በነጻ የሚገኙ ናቸው፣ ክፍያ አላቸው ተብለው ከተጠቀሱት ውጪ።

በተጨማሪም መሰል መመሪያዎችን በቻይንኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋ ማግኘት ይችላሉ። ሊያጋሩት የሚፈልጉት ተጨማሪ ነጥብ ካለ በኢሜይል አድራሻችን ይላኩልን


የምርመራ ጋዜጠኝነት

ዘመናዊ የምርመራ ጋዜጠኝነት ፤ በማርክ ሊ ሃንተር እና ሉክ ሴንገርስ፣ ከማርከስ ሊንድማን ጋር የተዘጋጀ። ይህም እንደ ስርዓተ ትምህርት ‹‹ተማሪዎች ሊጠይቋቸው የሚችሏቸውን ጥያቄዎች በማብራራት (መልሱን አብሮ በማያያዝ)፣ እንዲሁም ፈጠራ የታከለባቸው ምክክሮች እና ልምዶችን ያካተቱ የክፍል ሥራዎችንና የቤት ሥራዎች በመስጠት፣ ምን ማስተማር ይገባል ከሚለው ባለፈ፣ በዘርፉ ጀማሪ መምህራን እንዴት ማስተማር ይገባል የሚለውን የሚረዳቸው ነው።›› በ‹ስቶሪ ቤዝድ ኢንኳየሪ› (ከታች ይመልከቱ) ደራሲች የተዘጋጀ። እንዲሁም ከዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኮንፈረንስ-19 የገለጻ ገጾች መመልከት ይችላሉ።

የምርመራ ጋዜጠኝነት አሠራር መመሪያዎች ፤ ይህ ጠቃሚ መመሪያ ለአፍሪካ ጋዜጠኞች እንደ መምሪያ መጽሐፍ ሆኖ ነበር የጀመረው። በዛም ተግባራዊ ጥናቶች እና ልምምዶች የተካተቱበት ሲሆን፣ በጀርመኑ ‹ኮንራድ አዴኑዌር ስቲፍተንግ› ፋውንዴሽን የታተመ ነው። የመጨረሻው እትም ዓለማቀፍ ይዘት ያለው ሲሆን፣ ይህም ጨቋኝ የሚድያ ሕግ፣ የግልጽነት መጥፋትና የሀብት ውስንነት በሚኖር ጊዜ ዘጋቢዎች እንዲጠቀሙበት ተብሎ የተዘጋጀ ነው። በባህሳ እና ሞንጎልያን የሚገኝ ሲሆን፣ በመረጃ መለዋወጫ ድረ ገጽም ይገኛል።

በጥልቀት መመርመር/መቆፈር፡ በባልካን የምርመራ ጋዜጠኝነት መመሪያ ፤ ይህ መመሪያ በባልካን የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (BIRN) የታተመና ለገበያ የቀረበ ነው። ኔትወርኩ ትኩረቱን ያደረገው በክልሉ መዛግብትን እና መረጃዎችን እንዴት በጥልቀት መመልከት ይቻላል የሚለው ላይ ነው። ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የስታባይል የምርመራ ጋዜጠኝነት ማእከል ዳይሬክተር ደራሲ ሼሊያ ኮሮኔል የተገኙ ጠቃሚ የምርመራ አዘጋገብ ምክሮችና ዘዴዎችም ተካተዋል። የመጀመሪያውን ምዕራፍ በነጻ ያውርዱ። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛሜቄዶንያን

የምርመራ ጋዜጠኝነት መምሪያ መጽሐፍ (2020) ከአልጀዚራ የሚድያ ተቋም፤

Drehbuch der Recherche (የምርመራ ስክሪፕት) ፤ በማርክ ሊ ሀንተር እና ሉክ ሴገርስ የተዘጋጀ፣ በጀርመኑ ‹ Netzwerk Recherche› የታተመ። ቋንቋ – ጀርመን

እውነቱን ማጋለጥ፡ በአልቤንያ የምርመራ አዘጋገብ መመሪያ ፤ ይህ የ73 ገጽ መመሪያ የተለያዩ ጥናቶችን፣ ማረጋገጫ የተገኘላቸው ጠቃሚ ነጥቦችና ቴክኒኮችን ተጠቅሟል። በኦቼ እና በባልካን የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ የታተመ ነው። ቋንቋ – አልቤንያንኢንግሊዘኛ

The Hidden Scenario፣ በሉክ ሴንገርስ እና ማርክ ሊ ሀንተር የተዘጋጀ በ2019 የታተመ መጽሐፍ ነው። ይህም አንድን ኹነት መፍጠር ምርመራን ለማካሄድ ይረዳል የሚለው ላይ ያተኩራል። በምርመራ ጋዜጠኝነት ማእከል በኩል ለሽያጭ የቀረበ ነው።

Follow the Money: ሙስናን ለመከታተል የሚያስችል ዲጂታል መመሪያ ፤ ይህ ነጻ የመመሪያ መጽሐፍ በዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ማእከል የታተመ ነው። ቋንቋኢንግሊዘኛራሽያጆርጂያ

ዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኬዝ-ቡክ፡ ይሕ መጽሐፍ ‹ስቶሪ ቤዝድ ኢንኳየሪን› ያካተተ ነው። (ከታች ይመልከቱ) እነዚህ የምርመራ ዘገባዎች ጋር ተያይዞ ያለውን የጀርባ ታሪክ፣ ዘጋቢዎች እንዴት እንደተመራመሩና እንደጻፉ ይመረምራል። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

ዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት፤ የድጋፍ ስልቶች ፤ በዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርኩ ዴቪድ ካፕላን የተዘጋጀ የምርመራ ዘገባ በዓለማቀፍ ደረጃ መስፋፋቱን የሚመለከት ዳሰሳና ምክክር ሲሆን፣ ለትርፍ በማይሠራ የምርመራ ሥራ መዋቅርና የገንዘብ ምንጭ ዙሪያ ጠቃሚ ነጥቦችን የያዘ ነው። በተጨማሪም በዓለማቀፍ ደረጃ ለሚገኙ የምርመራ ቡድኖች መመሪያ ሆኖ ያገለግላል። ዓለማቀፉ የሚድያ ድጋፍ ሰጪ ማእከል ያሳተመው ነው። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Citizen Investigation Guide ፤ ይህ በ2019 በዓለማቀፉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ የተዘጋጀ መመሪያ፣ ዜጎች ምርመራ ዘገባዎችን እንዲሠሩ የሚረዳ ነው።

የምርመራ ጋዜጠኝነት መመሪያ ፤ ቀላልና በ2007 የወጣ፣ በአሜሪካ በሚገኘው የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎት የተዘጋጀ ነው። ይህም ዘጋቢው ታሪክን እንዴት መለየት እንዳለበት፣ እንዴት የምርመራ ቃለመጠይቅ እንደሚያደርግ፣ መረጃ እንዴት እንደሚሰበሰብና ለሕዝብ ተደራሽ እንደሚሆን ያመላክታል። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Hidden Scenario (ድብቅ ኹነት) ፤ ሉክ ሴንገርስ እና ማርክ ሊ ሃንተር ያዘጋጁት ነው። የታሪክ ነገራ ዘዴዎች እንዴት ቅርጽ እንደሚይዙና እንዴት የምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ያሳያል። (ለመግዛት በምርመራ ጋዜጠኝነት ማእከል ይገኛል) ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Introduction to Investigative Reporting፣ በብራን ሆስተን (ከፖይንተር የዜና ዩኒቨርሲቲ) የተዘጋጀ። በግል ማንቀሳቀስ የሚቻል የኦንላይን ትምህርት ሲሆን 29.95 የአሜሪካን ዶላር ክፍያ ይጠይቃል።

Investigating Religion: An Investigative Reporter’s Guide ፤ በዴብራ ሜሰን እና ኤሚ ዋይት (ከአይ.አር.ኢ. መግዛት ይቻላል) ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

የምርመራ ጋዜጠኝነት ማኑዋል ፤ የታተመው በአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኞች ፎረም (FAIR) ሲሆን፣ በርካታ ጠቃሚ ነጥቦችን ያካተተ እንዲሁም በጤና እና ሥነምግባር የተለየ ምዕራፍ ያለው ነው። እንዲሁም በአፍሪካ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶችን ያካተተ ነው። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛፈረንሳይኛ እና ፖርቹጊዝ

Investigative Journalist’s Guide to Company Accounts ፤ በራጅ ባይሮሊያ የተዘጋጀ። በምርመራ ጋዜጠኝነት ማእከል የታተመና በገበያ ላይ የሚገኝ፤ የኩባንያዎችን የሂሳብ ዝርዝር ትርጉም ለማግኘት የሚፈልጉ የምርመራ ጋዜጠኞችን የሚያግዝ (በንግድ የተሳተፉ ኩባንያዎች) ወይም ገንዘብ ነክ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ በንግድ ሥራ ዙሪያ ጠቅለል ያለ እይታ ለማግኘት የሚረዳ።

Investigative Online Search፣ ይህ መመሪያ፣ መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ባደረገው ምርመራ ጋዜጠኝነት ማእከል በ2011 የታተመ፣ አንድን መረጃ ኦንላይን እንዴት ማግኘት እንደሚቻልና እውነተኛቱን እንዴት ማረጋገጠ እንደሚቻል የሚያስረዳ ነው። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Investigative Photography: ታሪኮችን በምስል ማስደገፍ ፤ በክላርክ፣ ዴምየን ስፕሊተርስ እና ሉልዬት ፈርጉሰን የተዘጋጀ፣ (በምርመራ ጋዜጠኝነት ማእከል ለሽያጭ የሚገኝ)። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

የምርመራ ጋዜጠኞች መመሪያ መጽሐፍአምስተኛ እትም፣ በብራንት ሆስተን እና የምርመራ ዘጋቢዎችና ዋና አዘጋጆች የተሰናዳ። ይህም በአይ.አር.ኢ. ለሽያጭ ቀረበ ነው። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Investigative Reporting: A Toolkit for Reporters ፤ 107 ገጾች ያሉት በ2009 በአሜሪካ የግል ኢንተርፕራይዝ ማእከል የታተመና ለጋዜጠኝነት እንዲሁም ህትመት በዩ.ኤስ.አይድ እና አል – ማስሪ አልዩም የተደገፈ። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Investigative Reporting in Emerging Democracies: Models, Challenges, and Lessons Learned ፤ የተቀናበረ ወንጀልና ሙስና አዘጋገብ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሠራው ድሪው ሱሊቫን ያዘጋጀው ዘገባ ሲሆን፣ በዚህም ስለ ፕሮግራሞች ቅርጽ፣ ደረጃቸውን መጠበቅ፣ የዋና አዘጋጆች ሚና እና ደኅንነት አንዲሁም ተጨማሪ ሐሳቦችን አካቷል። በዓለማቀፍ የሚድያ ድጋፍ ማእከል የታተመ። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Manual for Arab Journalists on Freedom of Information and Investigative Reporting ፤ ነጻና ከኢንተርኔት በቀላሉ ማውረድ የሚቻል፣ 21 ገጾች ያሉት የመመሪያ መጽሐፍ ሲሆን 19 አንቀጾችን ይይዛል። የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ነው። ቋንቋኢንግሊዘኛአረብኛ

The News Initiative ፤ በጉግል የቀረበ ሲሆን፣ በምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ዘጠኝ ዘርፍ ያለው የትምህርት ዓይነት ያለው ነው፣ የጉግል መተግበሪያዎችን በመጠቀም፤

The Science Writers’ Investigative Reporting Handbook በሊዝ ግሮስ የተዘጋጀ የ2018 መጽሐፍ ሲሆን ከታሪኩ ጀርባ ያለውን ታሪክ እንዴት መመርመርና ማወቅ እንደሚቻል፣ ችግር ካለ ለመለየትና የተደበቀ መረጃን ለማግኘት የሚያግዝ።

Raising Hell: A Citizen’s Guide to the Fine Art of Investigation (PDF): በዓለማችን የመጀመሪያው ለትርፍ ያልተቋቋመ የምርመራ ዘገባ ማእከል የሆነው የምርመራ ዘገባ ማእከል፣ ይህን መመሪያ ያዘጋጀው፣ ጠቅላላውን ሕዝብ እንዴት መመርመር፣ ሙስናን ማጋልጥና የሥልጣንን ደካማ ጎን ማሳየት እንደሚቻል ለማሠልጠን ነው። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Recherche in der Praxis: Informanten zum Reden bringen, Fakten hart machen, Missstände aufdecken በካትሪን ቦስ እና ዶምኒክ ስትሬብል የተዘጋጀ ተግባራዊ ጥናት፣ ተሳታፊዎች እንዲናገሩ ማድረግ፣ ጠንካራ መረጃዎችን መያዝ እንዲሁም ጥቃቶችን ማጋለጥን ይመለከታል (ለግዢ ይገኛል)። ቋንቋ – ጀርመንኛ

Reporting in Indigenous Communities የካናዳ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዘጋቢ ዱንካን ማክዩ በ2011 የተጻፈ ነው። በዓለማቀፍ ደረጃ ጥንታዊ ሕዝቦችን ማካተት/ሽፋን መስጠት የሚያስችል መተግበሪያ አለው። የዘጋቢውን ቼክሊስት፣ ብሎግ እና ከማክዩ ጋር በ2018 የተደረገውን ቃለመጠይቅ ይመልከቱ፣

Story-Based Inquiry ፤ ለምርመራ ዘገባ የሚያግዝ ጠቅለል ያለ መመሪያ ሲሆን፣ ማርክ ሃንተር፣ ድሪው ሱሊቫን፣ ፒያ ቶስደን፣ ራና ሳባጅ እና ሉክ ሴንገርስ በጋራ የተዘጋጀ ነው። ይህ በዩኔስኮ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት መመሪያ፣ ዘዴዎችና መንገዶችን እንዲሁም ጥናቶችን፣ ጽሑፎችን፣ የጥራት ቁጥጥሮችን እና ስርጭትን ለማሳየት የተለያዩ ተግባራዊ ጥናቶችን ይጠቀማል። ቋንቋኢንግሊዘኛአረብኛቻይኒዝፈረንሳይኛራሽያኛፖርቹጊዝስፓኒሽ

The Story Tells the Facts, by Mark Lee Hunter and Luuk Sengers, ፤ በማርክ ሊ ሃንር እና ሉክ ሲንገርስ የተዘጋጀ ነው። (ከምርመራ ጋዜጠኝነት ማእከል በሽያጭ ይገኛል) የትረካ መንገዶችን ያብራራል፣ በዚህም በፍጥነትና በኃይል ተጽእኖ መፍጠር የሚችል ታሪክ እንዴት እንደሚዘጋጅና ጠንካራ መቋጫን እንዴት መገንባት እንደሚቻል ያብራራል። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Undercover Reporting ፤ መመሪያ አይደለም፣ ነገር ግን ኦንላይን የሚገኝ የመረጃ ቋትና የመረጃ ምንጭ ማእከል ነው። ይህም Undercover Reporting: The Truth About Deception ከተባለው የጥናት መጽሐፍ ውስጥ የተገኘ ነው። ይህም ከመቶ ዓመት በላይ እድሜ ያላቸውን ምሳሌዎች የያዘ ነው።

The Verification Guide for Investigative Journalists ፤ ዐስር ምዕራፎች እና ሦስት ጥናቶችን የያዘ ነው። በዚህ የተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮችም የኦንላይን መፈለጊያ መሣሪያዎች፣ መረጃ፣ በተጠቃሚ የሚንቀሳቀሱ ይዘቶች እና ሥነምግባር ናቸው። የThe Verification Handbook እና Verification Handbook: Additional Materials ጥምረት ነው። ይህን ለማውረድ ወይም ለመግዛት፣ ትርጉሙንም ለማግኘት ይህን ይጫኑ።

A Watchdog’s Guide to Investigative Reporting: ትኩረት የሚያደርገው በአፍሪካ ባለው ዘገባ ዙሪያ ነው። ይህ የ2005 የኢንግሊዘኛ ቋንቋ መመሪያ ‹ምሳሌ የሚሆኑ ጥሩ ተሞክሮዎችን ያቀርባል፣ የምርመራ ሥራዎችን ለመሥራ በጥርጣሬ ውስጥ ላሉትን በዘርፉ በሚኖረው ፈተና ዙሪያ የሚቃኝ ነው።


የመረጃ ጋዜጠኝነት

ለ30 ዓመታት ጋዜጠኞችን ስለመረጃ ጋዜጠኝነት ከማስተማር የተገኘ ትምህርት ፤ የዓለማቀፉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኮንፈረንስ-19 የተገኘ ጠቃሚ ነጥቦችን የያዘ ገጽ ሲሆን በብራንት ሆውስተን የተዘጋጀ ነው። ብራንት ሆውስተን በኢሊዮንስ ዩኒቨርሲቲ የ‹ናይት ቼር› የምርመራ ዘገባ ሊቀመንበር ናቸው። ከዐስር ዓመታት በላይ የምርመራ ዘጋቢዎችና አዘጋጆች ዋና መሪ በመሆን ሠርተዋል።

Teach Computational Thinking, Not Just Spreadsheets or Coding, የዓለማቀፉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኮንፈረንስ-19 የመረጃ ገጽ ሲሆን፣ ከበርሚንግሃም ሲቲ ዩኒቨርሲቲ/የቢቢሲ የመረጃ ክፍል ፖል ብራድሻው የተዘጋጀ።

7 countries, 9 teachers: a dossier of data journalism teaching strategies ተማሪዎችን ከመረጃዎች ጋር ለማስተዋወቅ በጣም ውጤታማ የሚባሉ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? በኖሃ ቤላይድ፣ አናስቴዠያ ቫሌቫ፣ ባሃሬህ ሄራቪ፣ ሮስሊን ዱ፣ ካይት ዴቪስ፣ አድሪያን ፒኖ፣ ኤድዋርድ ማርቲን ቦሬጎን፣ ሶሌዳድ አሬጉዌዝ እና ጄፍ ኬሊ የተዘጋጀ።

Data and Computational Journalism, ይህ የ2020 ጽሑፍ አራት ምክረ ሐሳቦችን የሚያቀርብ ነው። እነዚህም መምህራን በስርዓተ ትምህርት ውስጥ የመረጃና ጋዜጠኝነትን ትስስር አብረው እንዲያስኬዱ ለማስቻል ነው።የዚህ ጽሑፍ ደራስያን ኖርማን ልዊስ፣ ሚንዲ ማክአደምስ እና ፍሎሪያን ስታልፍ ናቸው። በዚህ ጽሑፍ የጠቀሷቸው አራት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፤

አንደኛ፣ ባሉ የትምህርት ዓይነት መጽሐፎች ላይ ወይም ለብቻው የሚገኝ ከቁጥር እና መሠረታዊ የቁጥር መረጃዎች ጋር በተገናኘ መመሪያ ሊኖር ይገባል። ኹለተኛ፣ በዘገባም ሆነ በምስል ክፍለ ጊዜዎች ተማሪዎች ስለ አንድ መረጃ ትርጓሜ ሲሰጡ ወይም ሲጽፉ ስህተትን እንዲያስወግዱ ሊማሩ ይገባል። ሦስተኛ፣ መረጃ ችግር ሊፈጥር የሚችል የግልጽነት መሣሪያ እንደሆነ የግብረገብ ትምህርቶች ሊያስረዱ ይገባል። አራተኛ፣ ኮምፕዩተር ችግሮችን በሚፈታበት መንገድ ነገሮችን እንዴት ተገንዝቦ መፍታት እንደሚቻል፣ ሎጂክ በሚያስተምሩ ነባሩ የትምህርት ክፍሎች ውስጥ ሊካተት ይችላል።

More Effective Teaching of Data Journalism to Working Journalists, በData-N ኩዋንግ ኬንግ የተዘጋጀና በዓለማቀፉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኮንፈረንስ-19 የቀረበ ነው። እነዚህ ጠቃሚ ነጥቦች ለዘርፉ አዲስ የሆኑና በሥራ ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን የመረጃ ጋዜጠኝነት የሚያስተምሩ አሠልጣኖችና መምህራንን ያለሙ ናቸው።

Hacking the curriculum: How to teach data reporting in journalism schools የ2018 የአሜሪካን የፕሬስ ተቋም ዘገባ። ‹‹የእኛ ዋና ምክረ ሐሳብ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤቶች የቁጥር መረጃዎችን ለሁሉም ተማሪዎች እንደ መሠረታዊ ብቃት እንዲያዩት ማድረግ ነው።

Where in the world can I study data journalism? ፤ ይህ ጽሑፍ በባሃሬህ ሔራቪ በ2019 የተዘጋጀ ነው። ጽሑፉ 3Ws of Data Journalism Education, published by Data Journalism Practice በሚል ርዕስ ያዘጋጀችውን ጥናታዊ ወረቀት አጠቃሎ የያዘ ነው። ይህን ወረቀት በUCD academic repository ማግኘት ይቻላል። እንዲሁም ካርታን ያካትታል።

International Journalism Education Consortium ፤ በኮምፕዩተር ለታገዘ እና ለመረጃ ጋዜጠኝነት የትምህርት ዓይነቶች የሚጠቅሙ ሊንኮችና ማብራሪዎች ያሉት ነው፤ (ዩኒቨርሲቲዎቹ ሥያሜ የአልፋቤት ተርታ ቀጥሎም በፕሮፌሰሮቹ ሥም የተቀመጠ)

Computer-Assisted Reporting: A Comprehensive Primer: በፍሬድ ቫላንስ ጆንስ እና ዴቪድ ማኪ (ለሽያጭ የቀረበ) ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Computer-Assisted Reporting: A Practical Guideበብራንት ሆስተን የተዘጋጀ አራተኛ እትም (ለሽያጭ የቀረበ) ቋንቋኢንግሊዘኛ

Computer-Assisted Research: Information Strategies and Tools for Journalistsበኖራ ፖል እና ካትሊን ሃንሰን የተዘጋጀ፣ (በአይ.አር.ኢ ለሽያጭ የቀረበ) ቋንቋኢንግሊዘኛ

Data Journalism Handbook በርካታ የመረጋ ጋዜጠኝነት ባለሞያዎችን ያካተተ ዓለማቀፍ የተባበረ ጥረት ነው። ትርጓሜ፣ የተደረጉ ጥናቶችና ጠቃሚ ነጥቦች የተካተቱበት ሲሆን እነዚህም መረጃን እንዴት ማግኘት፣ መጠቀምና መተንተን ይገባል የሚለውን ያካትታል። በአውሮፓ የጋዜጠኝነት ማእከል እና የኦፕን ኖውሌጅ ፋውንዴሽን ያስጀመሩት ነው። ቋንቋ – ከኢንተርኔት ለማውረድ የሚቻል ሲሆን፣ በአረብኛኢንግሊዘኛፈረንሳይኛሩስያኛ እንዲሁም በስፓኒሽ ይገኛል። ይህ የመመሪያ መጽሐፍ ከዚህ በተጨማሪም ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች እየተተረጎመ ነው። ከዚህም ውስጥ ጆርጂያን ይገኝበታል። የ2012 እትም ወደ 12 በላይ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ነበር። ከእነዚህም አረብኛ፣ ቻይኒዝ፣ ቼክ፣ ፈረንሳይ፣ ጆርጂያን፣ ግሪክ፣ ጣልያንኛ፣ ሜቄዶንያን፣ ፖርቹጊዝ፣ ሩስያኛ፣ ስፓኒሽ እና ዩክሬንያን ይጠቀሳሉ።

Flowing Data ናታን ዩን በተባለው የስታትስቲክስ ባለሞያ የሚመራ ሲሆን፣ ናታን የData Points: Visualization that Means Something እና Visualize This: The FlowingData Guide to Design, Visualization, and Statistics ደራሲ ነው። ይህ የመረጃ ነክ ትምህርት ቋት የተለያዩ ከመረጃ ጋር መሥራት ጋር የተገናኙ ሥልጠናዎች፣ መጽሐፎችና መመሪያዎች የሚገኙባቸው ሊንኮች ይገኙበታል።

Mapping for Stories: A Computer-Assisted Reporting Guide, በጄኒፈር ላፍሎር እና አንዲ ሌህረን የተዘጋጀ፣ በአይ.አር.ኢ ለሽያጭ የሚገኝ ነው። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Precision Journalism: a Reporter’s Introduction to Social Science Methods, በፊሊፕ ሜየር የተዛጋጀ፣ በሽያጭ ላይ የሚገኝ። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Datawrapper የወርክሾፕ አስፈላጊ ቁሳቁሶች

በጠቅላላ የጋዜጠኝነት የመረጃ ምንጮች ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የመረጃ ጋዜጠኝነት ምንጮች ገጽን ይመልከቱ፣


ትምህርት እና ሥልጠና

Model Curricula for Journalism Education ፤ ይህ መመሪያ ዓላማ ያደረገው በአዳጊ አገራት ያሉ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍሎችን እና አዳዲስ ዴሞክራሲ የሚለማመዱትን ነው። በዩኔስኮ የዳበረው ይህ መመሪያ፣ እያንዳንዱ አገር የሚያስፈልገው ምንድን ነው የሚለውን ታሳቢ በማድረግ፣ የ17 የትምህርት ዓይነቶችን ማስተማሪያ ስርዓተ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ይህም የምርመራ ዘገባን ያካትታል። ቋንቋኢንግሊዘኛፈረንሳይኛስፓኒሽሩስያኛአረብኛቻይኒዝኔፓሊፖርቹጊዝፋርሲ

International Journalism Education Consortium ፤ የምርመራ ጋዜጠኝነት ትምህርቶች ማብራሪያ እና ለምርመራ ጋዜጠኝኘት የትምህርት ዓይነቶች ማስተማሪያ ስርዓት/መመሪያ ነው። (በዩኒቨርሲቲዎች ሥያሜ የመጀመሪያ ፊደል ተርታ እናም በፕሮፌሰሮች ሥም)

The James W. Foley Journalist Safety Guide: A Curriculum Plan For College Journalism and Communications Instructors ፤ ለአምስት ተከታታይ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚሆን የተብራራ እቅድ የያዘ ነው። በተወሰነ ደረጃ መነሻ ያደረገውም ሚያዝያ 19 ቀን 2014 ሶርያ ውስጥ በተገደለውን ጋዜጠኛ ጄምስ ፎሌይ ዙሪያ ኤችቢኦ የሠራውን ዘጋቢ ፊልም ነው። በስርዓተ ትምህርቱ ተጨማሪ ማጣቀሻዎች የሚገኙ ሲሆን፣ ይልቁንም አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ስለመሥራ የተለያዩ ዘጋቢዎች የጻፏቸው ጽሑፎች ይገኙበታል። ኹነቶች የተብራሩ ሲሆን ጥያቄዎችም ተተንትዋል። ይህን ካሪኩለም ‹FoleySafety› በሚል ይለፍ ቃል ማግኘት ይችላሉ።

Algorithms for Journalists: የማስተማርያ ዝርዝር እቅድ ሲሆን፣ ይህም በኮሎምቢያ የጋዜጠኝነት ትምህርት የሊድ ፕሮግራም መምህር በሆነው ጋዜጠኛ ጆናታን ስትሬይ የሚሰጥ ትምህርት ነው። ይህም በ‹GitHub› የሚገኝ ሲሆን፣ በዛም ተያያዥ ሊንኮች፣ የሚነበቡ መጻሕፍትና መልመጃዎች አሉ። ይህም በፕሮግራሙ ጀማሪ ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ የትምህርት ክፍለ ጊዜ እንደሆነ ልብ ይሏል!

Better News በአሜሪካ ፕሬስ ተቋም የሚመራ ድረገጽ ሲሆን በርካታ ምንጮች ይገኙበታል፤

AEJMC Task Force for Bridges to the Professions 2017 Report ፤ በጋዜጠኝነት እና የብዙኀን መገናኛ ትምህርት ማኅበር (AEJMC) በሚገኙ ጋዜጠኞችና የትምህርት ባለሞያዎች መካከል ያለውን ትብብር በሚመለከት የወጣ የ2017 ዘገባ።

Observations on how we teach drone journalism, በጁድ ስሊቭካ፣ በሚዝሪ የጋዜጠኝኘት ትምህርት ቤት የመጀመሪያ የኤሪያል ጋዜጠኝነት ዳይሬክተር

Algorithms course materials at Columbia Journalism School ፤ የማስተማሪያ አሠራርና ስርዓት በኮሎምቢያው ፕሮፌሰር ጆናታን ስትሬይ የተዘጋጀ፤

The Field Guide to Security Training ፤ በኦፕን ኒውስ የሚመራ ስርዓተ ትምህርት ነው፤ ይህም ዴቨሎፐሮችን፣ ዲዛይነርና የመረጃ ተንታኞችን የሚያግዝ እና ግልጽ የሆኑ የጋዜጠኝነት ፕሮጀክቶችን የሚያስተባብር ቡድን ነው። እንዲሁም BuzzFeed Open Lab የሚባለው በተጓዳኝ የጥበብና የቴክኖሎጂ ሐሳብ መለዋወጫ ነው፣ በበዝፊድ ኒውስ።

Dig Deep & Aim High፤ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ማእከል በ2000 ያሳተመው መመሪያ ሲሆን ይህም የምርመራ ዘዴዎችን እንዴት ማስተማር ይቻላል የሚለውን የሚያሳይ ነው፤ ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ


ተጨማሪ ጠቃሚ መመሪያዎች

Empowering Independent Media: U.S. Efforts to Foster a Free Press and an Open Internet Around the World: ፤ ጠቅለል ያለ የሚድያ ልማትን የሚያስቃኝ ነው። ይህም ለትርፍ ላልተቋቋሙ ሚድያዎች እና በአዳጊ አገራት ለሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚጠቅም ነው። ሰባት ወሳኝ የሚድያ ልማት ዘርፎችን የሚሸፍን ሲሆን፣ እነዚህም ገንዘብ፣ ዲጂታል ሚድያ፣ ዘላቂነት፣ የሚድያ ሕግ፣ ደኅንነት፣ ትምህርትና ክትትል እንዲሁም ምዘና ናቸው። ቋንቋኢንግሊዘኛስፓኒሽፈረንሳይኛ

Google Search Tips for Journalists: ፤ ይህ አጭር በቀላል የሚያዝ መመሪያ ሲሆን፣ የጉግል መፈለጊያ መተግባሪያዎችን በመጠቀም የተሻሉ የፍለጋ ውጤቶችን ያስገኛል። በExpertisefinder.com የተሰባሰበ ነው።

Journalist Survival Guide ፤ መቀመጫውን ቤሩት ባደረገው ሳሚር ካሲር ፋውንዴሽን ወጪ የተደረገበት ነው፣ በጦርነት አካባቢዎች እና ግጭት ባለባቸው ስፍራዎች ያሉ ጋዜጠኞችን ለማገዝ ነው በዋናነት የተዘጋጀው። እንዲሁም ደግሞ ዲጂታል ሴክዩሪቲ እና ዱካን መሸፈን ላይ ተጨማሪ ነጥቦችን ያካተተ ነው። ቋንቋኢንግሊዘኛአረብኛ

Legal Leaks Toolkit: A Guide for Journalists on How To Access Government Information ፤ የ75 ገጽ ቡክሌት ነው፣ መንግሥታዊ ሰነዶችን ለማግኘት መደበኛ በሆነ መንገድ ለሚሄዱ ጋዜጠኞች መሠረታዊ ጉዳዮችን ይሸፍናል። የተዘጋጀው በ‹አክሰስ ኢንፎ ኢውሮፕ› እና በ Network for Reporting on Eastern Europe n-ost ነው። በኢንግሊዘኛጣልያንኛ እንዲሁም በስምንት የምሥራቅ አውሮፓ ቋንቋዎች ይገኛል።

Reporting Atrocities: A Toolbox for Journalists Covering Violent Conflict and Atrocities: ፤ የተብራራና 61 ገጾች ያሉት መመሪያ ነው፣ የግጭትን መነሻ የሚመለከት ሲሆን እንዲህ ያሉ ኹነቶችን እንዴት የዘገባ ሽፋን እንደሚሰጥ እንዲሁም እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ የጋዜጠኞችን ድርሻ የሚያስቃኝ ነው። በደቡብ አፍሪካዊው ጋዜጠኛ ፒተር ዱ ቶይት ተጽፎ በኢንተርኒውስ የታተመ ነው። ቋንቋ – ኢንግሊዘኛ

Reporting on Corruption: A Resource Tool for Governments and Journalists ፤ ይህ በተባበሩት መንግሥታት የአደገኛ እጽ እና ወንጀል ቢሮ የተዘጋጀ የ117 ገጽ መመሪያ በተለያዩ የቢሮክራሲ አሠራሮች ምክንያት ቢዘገይም፣ ጠቃሚ ጥናቶችን እና ምንጮችን አካትቷል። የምንጮችን ደኅንነት፣ መረጃ የማግኘት ነጻነትን ያካተተ ነው።

SEEMO Safety Net Manual: Guidelines for Journalists in Extraordinary or Emergency Situations ፤ ይህ የደኅንነት መመሪያ በሰሜን ምሥራቅ የአውሮፓ የሚድያ ተቋም የታተመ ሲሆን፣ በአካባቢው ያሉ የመገናኛ ብዙኀን ሠራተኞችን ለመጠበቅ ከታሰበው ሰፊ ንቅናቄ አንድ አካል ነው። ቋንቋኢንግሊዘኛ እና በቀረበ ጥያቄ መሠረት ሰርቢያን፣ ጣልያንኛ፣ ግሪክ፣ ሮማንያን፣ ቱርኪሽ፣ ቡልጋርያን፣ ክሮሽን እና ስሎቬንያን የቀረበ፤

Tragedies & Journalists ፤ 40 ገጽ መመሪያ ሲሆን ለተግባር ምቹ የሆኑ ጠቃሚ ነጥቦች አሉት። ይህም ጋዜጠኞች፣ የፎቶ ጋዜጠኞች እና አዘጋጆች ጥቃት ሲከሰት ራሳቸውንም ሆነ ሌሎችን እንዲጠብቁ ሪፖርት የሚያደርጉበት ነው። በዳርት የጋዜጠኝነትና ትራውማ ማእከል የታተመና፣ በጆዊ ሃይት እና ፍራንክ ስሚዝ የታተመ ነው። ቋንቋኢንግሊዘኛስፓኒሽቻይንኛ

Verification Handbook ፤ ለጋዜጠኞችና ድጋፍ ሰጪዎች እንደ ምንጭ የሚያገለግልና በአውሮፓ የጋዜጠኝነት ማእከል የቀረበ ነው። በተጠቃሚ የሚሠራና ይዘትን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ መሣሪያ፣ ዘዴ እና ደረጃ በደረጃ ሂደቱን የሚያሳይ መመሪያ የያዘ ነው፤ በድንገተኛ ጊዜ። ቋንቋኢንግሊዘኛፖርቹጊዝኢስፓኞል

Who’s Running the Company: A Guide to Reporting on Corporate Governance ፤ በኮርፖሬት አመራር ዙሪያ የሚደረግ ዘገባን ለማድረግ የሚያግዝ ሲሆን፣ ይህም በምዕራፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የሂሳብ ዘገባዎች እና የኩባንያውን አፈጻጸም በጊዜ ሂደት ያስቀምጣል። ዓለም ባንክ ዓለማቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን እና በዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ማእከል ትብብር የተዘጋጀ ነው። ቋንቋኢንግሊዘኛፈረንሳይኛስፓኒሽባህሳ – ኢንዶኔዥያሞንጎሊያንአረብኛሩስያ እና ፖርቹጊዝ

Security and Covering Conflict: ፤ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ኔትወርክ ለጋዜጠኞች ደኅንነትና የግጭት አዘጋገብ መመሪያ ዝርዝሮችን ከተለያ ተቋማት የተገኙ መመሪያዎችን ዝርዝር አሰባስቧል። ከእነዚህም አንዳንዶቹ በተለያየ ቋንቋ የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም አረብኛ፣ ቻይንኛ፣ ራሽያኛ እና ስፓኒሽ ይገኙበታል።


በስፓኒሽ ብቻ

ተከታዮቹ መመሪዎች በስፓኒሽ ቋንቋ ብቻ የሚገኙ ናቸው። ከላይ የተቀመጡትን ዘገባዎችም ተመልከቱ፣ አብዛኞቹ በስፓኒሽ ቋንቋ የታተሙ ናቸው። እንዲሁም ይህ ሙሉ ገጽ በስፓኒሽ ቋንቋ ይገኛል፤

Cómo Investigar Temas Ambientales  ፤ (የአካባቢያዊ ጉዳዮች ምርመራ) በደቡብ አፍሪካ አካባቢያዊ ጉዳዮችን ለመመርመር የሚረዳ መመሪያ፣

Guía Práctica sobre Periodismo de Datos ፤ (ለመረጃ ጋዜጠኝነት የሚረዳ ተግባራዊ መመሪያ) የናይት ዓለማቀፍ ጋዜጠኝነት ኅብረት አባል፣ በሳንድራ ክሩሲኔሊ የተዘጋጀ። ይህ መመሪያ መረጃን ወደ ምስል መቀየር የሚቻልበትን ጠቃሚ ነጥብ የሚያቀርብ መመሪያ ነው፣ እንዲሁም በመረጃ ጋዜጠኝነት ላይ የሚሠሩ ዘጋቢዎችን መሠረት ያደረጉ ጥናቶችን ይዳስሳል። በዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ማእከል የታተመ ነው።

Manual de Periodismo de Datos Iberoamericano ፤ (የላቲን አሜሪካ የመረጃ ጋዜጠኝነት መመሪያ መጽሐፍ) መረጃ መፈልፈልና ማግኘት፣ ጥልቅ የድረ ገጽ ፍለጋ፣ መረጃን ወደ ምስል መቀየርና ሌላውንም በተመለከተ ጠቃሚ ነጥቦችና ትምህርቶችን ያቀርባል። ይህ ለስፓኒሽ ተናጋሪ ዘጋቢዎች የሚያግዝ መመሪያ በፖዴሮሚድያ ፋውንዴሽን የታተመ ሲሆን፣ በአልቤርቶ ሁርታዶ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ነው።

Métodos de la Impertinencia (Methods of Impertinence) ፤ ይህ የቬንዝዌላ የፕሬስና ማኅበረሰብ ተቋም አንድ አካል ሲሆን፣ በላቲን አሜሪካ ያሉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ምርጥ ተሞክሮና ትምህርቶች ስብስብን ይፋ ያደረገ ነው። በአካባው ካሉ ዐስር ተጽዕኖ ፈጣሪ ጋዜጠኞች ቃል የተሰበሰበበት መጽሐፍ ነው።

Periodismo de Investigacion (የምርመራ ጋዜጠኝነት) በጄራርዶ ሬይስ የተዘጋጀ፤ በላቲን አሜሪካ የምርመራ ዘገባ ጠቅለል ያለ ማብራሪያ ነው። ይህም እቅዶችና እና ስልቶችን ያካተተ ነው።

Periodista de Investigacion Latinoamericano en la Era Digital (የላቲን አሜሪካ ጋዜጠኛ፤ የዲጂታል ዘመን ጥናት) ፤ ይህ የተዘጋጀው በአሜሪካ የጋዜጠኝነት ጥናት ንቅናቄ እና በዓለማቀፉ የጋዜጠኝነት ማእከል (ICFJ)፣ ከ Connectas ጋር በመተባበር ነው። ናታሊያ ሳላማንካ፣ ጆርጅ ሲሪ እና ካርሎስ ኤድዋርዶ ሁዌርታስ በተባባሪ ጸሐፊነት ተሳትፈዋል።

Republish our articles for free, online or in print, under a Creative Commons license.

Republish this article


Material from GIJN’s website is generally available for republication under a Creative Commons Attribution-NonCommercial 4.0 International license. Images usually are published under a different license, so we advise you to use alternatives or contact us regarding permission. Here are our full terms for republication. You must credit the author, link to the original story, and name GIJN as the first publisher. For any queries or to send us a courtesy republication note, write to hello@gijn.org.

Read Next

የናይጄሪያው ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) በኮቪድ 19 ምላሽ ተጠሪነትን ለመፍጠር እያደረገ ያለው ግፊት

መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።