ሃብት ጠቃሚ ምክር
የምርመራ ጋዜጠኝነት መመሪያዎች
ጠቃሚ ነጥቦች፣ መሣሪያዎችና ተጨማሪ ሥልጠናዎችን እየፈለጉ ነው? ከታች የሚታዩት መመሪያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ ተጨባጭ ጥናቶችን እና ምሳሌዎችን ያቀርባሉ። አብዛኞቹ በነጻ የሚገኙ ናቸው፣ ክፍያ አላቸው ተብለው ከተጠቀሱት ውጪ።
ጠቃሚ ነጥቦች፣ መሣሪያዎችና ተጨማሪ ሥልጠናዎችን እየፈለጉ ነው? ከታች የሚታዩት መመሪያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ ተጨባጭ ጥናቶችን እና ምሳሌዎችን ያቀርባሉ። አብዛኞቹ በነጻ የሚገኙ ናቸው፣ ክፍያ አላቸው ተብለው ከተጠቀሱት ውጪ።
መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።
የምርመራ ዘገባ ሥራ ሁልጊዜም ውድ ነው። ዘርፉ በዓለም ደረጃ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ በገባበት በዚህ ጊዜ፣ በርካታ የሚባሉ የንግድ//ኮሜርሻል ሚድያዎች ግንዘብን እንደወትሮው ለምርመራ ዘገባ አይመድቡም።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ በኮቪድ 19 ዙሪያ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በሚመለከት ለኅብረቱ ንግግር ሲያደርጉ፤