Accessibility Settings

color options

monochrome muted color dark

reading tools

isolation ruler

Taswira: ICIR

ሪፖርት ማድረግ

የናይጄሪያው ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) በኮቪድ 19 ምላሽ ተጠሪነትን ለመፍጠር እያደረገ ያለው ግፊት

Read this article in

የዓለማቀፉ የምርመራ አዘጋገብ ማእከል ዳዮ አይታን ዓለማቀፍ የምርመራ አዘጋገብ ማእከል

መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።

ላለፉት (ስድስት) ሳምንታት በኮቪድ 19 ዙሪያ የተለያዩ የምርመራ ሪፖርቶችን ሠርተሃል። ከእነዚህ ዘገባዎችህ መካከል በጣም በከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠር ችለዋል የምትላቸው የትኞቹ ናቸው?

የመጀመሪያው ነው ብዬ የማምነው በቁጥር መረጃዎች ላይ መሠረት ያደረገ ዘገባ ሲሆን፣ ይህም የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ የናይጄሪያ ቤተሰቦች ይሰጣል የተባለው የገንዘብ ድጋፍን የመረመርንበት ነበር። የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት 20 ሺሕ የናይጄሪያ ናራ ወይም 51 ዶላር በአገር አቀፉ ማኅበራዊ መዛግብት ማህድር መረጃ ላይ ተመስርቶ በጣም ድሃ ለሆኑ ቤተሰቦች እንዲሰጥ አዘው ነበር።

ነገር ግን የምርመራ ሪፖርታችን እንደሚያስረዳው በብሄራዊ መዛግብቱ ላይ ካሉት እና እርዳታው እንዲሰጣቸው ከተወሰኑት ቤተሰቦች ውስጥ ከግማሽ የሚያንሱት ብቻ ነበሩ ድጋፉን እያገኙ የነበሩት።

መረጃዎች እንደጠቆሙን ከሆኑ የገንዘብ አሰጣጡ አሻሚነት የተነሳ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ነዋሪዎች በደቡባዊው ከሚገኙ ክልሎች እጅግ የበለጠ ድጋፍ ሲያገኙ ነበር። በዚህም መንግሥት የተሻለ የተመጣጠነ የምግብ እርዳታን የማከፋፈያ መንገድ እንዲጠቀም እና ይህም በተቻለ መጠን በቁጥር የላቁ ናይጄሪያውያንን እንዲያካትት እንዲያደርግ ያስገደደው ነው።

ምስል፤ ዓለማቀፍ የምርመራ አዘጋገብ ማእከል

ሌላው ዶክተሮች እና ሌሎች የጤና ባለሞያዎች የሚያገኙት የአደጋ ጊዜ ክፍያን የተመለከተው ዘገባችን ነበር። በአንዳንድ አካባቢዎች ዶክተሮች በወር እስከ 13.64 ዶላር ዝቅ የሚል ክፍያን ያገኛሉ። ይህንን በሌሎች የምዕራብ አፍሪካ አገራት ከሚከፈለው የአደጋ ጊዜ ክፍያ ጋር አነፃፅረነው ነበር። በጋና 361 ዶላር፣ በሴራሊዮን 460 ዶላር እንዲሁም በላይቤሪያ ደግሞ 825 ዶላር ሐኪሞች በወር የአደጋ ጊዜ ከፍያ ይከፈላቸዋል። እናም ይህን ዘገባ በሠራን በሳምንታት ውስጥ የክልልና የፌዴራሉ መንግሥትታት ሁኔታውን ሊቀይሩት ችለዋል።

በኔ እይታ፣ ዘገባችን ትልቅ ጫና የነበረው፣ በተለይ ናይጄሪያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ለምታደርገው ፍልሚያ ያላትን ዝግጅት አጋነው የገለፁትን የጤና ሚኒስትር በማጋለጡ ነው። የጤና ሚኒስትሩ በሌጎስ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ጎብኝቶ ናይጄሪያ ኮሮና ቫይረስን ለመፋለም ዝግጁ ናት ብሎ አውጆ ነበር። የዓለም የጤና ድርጅትም ተመሳሳይ ሐሳብ ሲያቀነቅን ነበር።

ነገር ግን የኛ የምርመራ ሪፖርት ናይጄሪያ በቂ የለይቶ ማቆያ ማእከላት እንኳን እንደሌላት እና ወረርሽኙ ይዞት ለሚመጣው ቀውስ ዝግጁ ያለመሆን የሚያሳይ ነበር። በኔ እምነት እኛ ሚኒስትሩን ማጋለጣችን ለመንግሥት አዲስ መንግሥታዊ ስትራቴጂ ግብዓት ሆኗል። ከዛም በኋላ የተሻለ ግልፅነት ያለው እና ታማኝነት ያለውን መረጃ ለናይጄሪያዊያን የሚቀርበት ሆኗል። አሁን የፕሬዝዳንቱ የኮቪድ 19 ግብረ ኃይል በየቀኑ መግለጫዎችን ይሰጣል።

የኮሮና ቫይረስ በመላው ዓለም ከመንሰራፋቱ በፊት በቅድሚያ የጤና ዘገባ ብቻ ሆኖ ነበር ሲወጣ የነበረው። እንደ አንድ የተለያዩ አይነት ያላቸውን ዘጋዎች የሚሠሩ ቡድኖችና ዘጋቢዎች እንዳለው የምርመራ ዘገባ ክፍል፣ ተጽእኖ ሊፈጥር በሚችል መልኩ እንዴት ነበር ቡድናችሁ በኮቪድ ዙሪያ ዘገባዎችን ይሠራ የነበረው?

ተቋማችን አነስተኛ የሚባል የዜና ክፍል ነው የሚያስተዳድረው። በዋና ከተማዋ አቡጃ እንጂ በክልሎች ዘጋቢዎች የሉንም። በዋና ከተማ ደግሞ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎ ነበር። ለዚህ ጋዜጠኞቻችን በተለያየ አካባቢ ሆነው ነበር ዘገባዎቻቸውን ሲልኩልን የነበሩት፣ ይህም በመላው የፌደራል ክልል ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደነበር ሰፊ እይታ የሰጠን ነበር።

በመላው አገሪቱ የተለያዩ ነገሮች እየተካሄዱ ነበር። ቢሆንም እኛ ግን ያንን መሸፈን አልቻልንም ነበር። ስለዚህ ይህንን ለመፍታት በተለያዩ የአገሪቱ ከፍ ካሉ በምርመራ ፕሮጀክቶችን ላይ አብረን የሠራናቸውን ጋዜጠኞች በማፈላለግ በተወሰኑ ጉዳች ላይ አብረን በመሥራት እና በጋራ ዘገባዎቻችን ስናሳትፍም ነበር። ይህም በተለይ በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት መንግሥት ለቫይረሱ ሲሰጥ የነበረው ምላሽ፣ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ሲገኙ መሸፈን እና መካድ እንዲሁም አስተዳደር ጉድለት ያለባቸው የቫይረሱ መከላከል ሁኔታ ላይ ከተለያየ አንጻር በተለያየ መንገድ ዘገባዎችን ስንሠራ ነበር።

የእንቅስቃሴ ገደብ በነበረበት ወቅት ከሠራሃቸው ወይም ከሠራችኋቸው የምርመራ ዘገባዎች የተወሰኑትን ልታካፍለን ብትችል፣ በተያያዘም እንዴት እንደተሠሩ ብታብራራልን?

በእስር ቤቶች ያለውን መተፋፈግና መጨናነቅ እንዲሁም ተያይዞ የወረርሽኙን ስርጭት ስጋት በሚመለከት፣ ቢያንስ በናይጄሪያ በአንድ ማረሚያ ቤት ዙሪያ ምስጢራዊ ዘገባ ሠርተናል። ዝርዝሩን እዚህ ማንሳት አልችልም፣ ነገር ግን ዘጋቢያችን ማይዱጉሪ የሚባለው ከፍተኛ ጥበቃ ያለበት እስር ቤት በመግባት፣ መጨናነቁ ካልቀነሰና ለጥንቃቄ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ለእስረኞች ካልተሟሉ፣ ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ማሳየት ችሏል።

ሌላው የሠራነው ምርመራ አክዋ ኢሞም በሚባለው ክልል የሚገኘው መንግሥት ለወረርሽኙ የሰጠውን ምላሽ በሚመለከት ነው። እየሆነ ያለውን ካወቅን በኋላ አንድ ዘገባ የሚያቀብለን የሚታመን ጋዜጠኛ ከዛው ክልል አግኝተን ነበር። ይህ ምርመራ አስፈላጊ የሆነው የክልሉ መንግሥት መረጃዎችንና የኮቪድ ምርመራዎችን በመደበቅ/ባለመስጠት እና የሕክምና ባለሞያዎችን በማስቆጣት ብዙ ክህደት እየፈጸመ ስለነበር ነው። ምርመራውም ያንን ሁሉ ይፋ አውጥቷል።

እዚህ ላይ ደስ የሚለው ነገር፣ የክልሉ መንግሥት አንድ ባለሥልጣን በወረርሽኙ ዙሪያ የእኛን ዘገባዎች ይከታተል ነበርና፣ ከአክዋ ኢቦም ስቴት ድረስ እየሆነ ስላለው መረጃ ሊያቀብለን ወደ እኛ መጥቷል። በቦታው ዘጋቢ አልነበረንምና፣ ዘገባውን የሚሠራ ታማኝ ጋዜጠኛ አገኘን፣ ይህም ወደ ምንጮቻችን ቅርብ አድርጎናል። ምንጮችን በቀላል ለማግኘት ረድቶታል።

የኮቪድ 19 ጉዳዮችን በመዘገብ ረገድ ለብዙ ጋዜጠኖች ፈተና ነበረው የቁጥሮች ተዓማኒነት ነው። አንተና የምርመራ ቡድኑ እንዲህ ያሉ ፈተናዎች ገጥሟችኋል? እንዴትስ ልትወጡት ቻላችሁ?

በፍጥነት ወደ አእምሮዬ የመጣው በድሆች ማኅበራዊ ጉዳይ ዘገባ ላይ የሠራነው ኹነት ነው። መንግሥት ትክክለኛውን የአባወራ ቁጥር አይናገርም ነበር። ጋዜጠኞችን ጨምሮ ብዙ ሰዎችም ማረጋገጫ ሊገኝላቸው የማይችል የተለያዩ ቁጥሮችን ሲጠቅሱ ነበር።

እድለኛ ነበርን። ፍለጋችንን ቀጥለን በመጨረሻ ከመንግሥት ሰነድ መረጃዎችን የሚያቀብለን ትክክለኛውን ምንጭ ከትክክለኛው ቦታ አገኘን። ሰነዱ እውነተኛ መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ፣ ቁጥሮቹን ተከትለን ተመለከትን። ይህንን መንግሥትም መካድ አልቻለም ነበር።

በወረርሽኙ ጊዜ የምርመራ ዘገባ ስትሠሩ የገጠማችሁ ትልቁ ፈተና ምን ነበር?

በእኔ እምነት ትልቁ ፈተና የነበረው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ትግል በሚደረግባቸው ግንባሮች ይልቁንም ከሆስፒታሎችና ለይቶ ማቆያዎች ሆነን ስንዘግብ የሚገጥመን ስጋትና ጭንቀት ነው። የጤና ባለሞያዎችን በሚመለከት ዘገባዎችን መሥራትና ታሪኮችን ማሰማት ፈልገን ነበር። የኮቪድ 19 ሕሙማንን በማከም እንዴት እንደተቋቋሙ፣ ምን ዓይነት ጥቅም እያገኙ እንደሆነ፣ ራሳቸውን ለመጠበቅ የሚያስችል በቂ የመከላከያ ቁሳቁስና የሕክምና መሣሪያ ተሟልቶላቸው እንደሆነ ልንመለከት ፈልገን ነበር።

ሆኖም መንግሥት ገብተን እንዳንሠራ ዕድሉን ወይም ፈቃድ ከለከለን። ምንም እንኳ እነዛ ታሪኮች ሊነገሩ የሚገባ ቢሆንም፣ መንግሥት በኮቪድ 19 ታማሚዎች ሕክምና ለመስጠት ያሉ እጥሮች ይፋ እንዲወጡ እንደማይፈልግ ይገባናል።

ሌላው ፈተና የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ ሰሞን የነበሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መዘገብ ነው። አብዛኞቹ ጋዜጠኞቻችን መኪና የሌላቸው በመሆኑ፣ አንዳንዴ በፈለግነው ስፋት መጠን አንድን ኹነት እንዳንናገር እንገደባለን። ሆኖም ከእነዚህ ክስተቶች በቶሎ ተምረን ከኹኔታዎች ጋር አብሮ ለመሄድ የሚያስችል ልምድ አዳብረናል።

በወረርሽኙ ሰሞን ምርመራዎችን ለማካሄድ በምታደርጉት ጥረት ያገዛችሁ ወይም ግብዓት የሆናችሁ ይህ ነው የሚባል መሣሪያ ወይም ግብዓት አለ?

አንዳንዴ የምንጠቀማቸው መሣሪያዎች በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ እንደ ‹ትዊተር› ወይም ‹ትሩ-ኮለር› እና ‹ዌይባክ ማሽን› ያሉ መተግበሪያዎች ይሆናሉ። አንዳንድ ዘገባዎችን ለማጣራት ደግሞ፣ በእርግጥ ብዙ ነበሩ፣ ‹ቲን አይ› እና ‹ጎግል ሪቨርስ› የምስል መፈለጊያዎችን እንጠቀም ነበር። የወረርሽኙ የመጀመሪያ ሰሞን እንዲሁም ከእንቅስቃሴ ገደብና የአየር መንገዶች መዘጋጋት በኋላ፣ በረራዎችን ለመከታተል ‹Flightradar24› እንጠቀም ነበር።

ለምሳሌ፣ በኋላ በኮቪድ 19 ምክንያት ሕይወቱ እንዳለፈ የተሰማው የቀድሞ የናይሪጄያ የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አባ ኪያሪን የት እንዳለ በምናጣራ ጊዜ፣ ከአቡጃ የወጣባቸውን ጊዜያትና የት እንደሄደ ለማጣራት በረራ ያደረገባቸውን ቀናት ለማግኘት ሞክረን ነበር።

የምርመራ ጋዜጠኞች እንዳይዘነጉና እንዲያስታውሱ የምትፈልገው፣ በአንጻሩ ያመለጡ ናቸው የምትላቸው አጋጣሚዎች ወይም እድሎች የትኞቹ ናቸው?

መረጃዎችን መንግሥትን ተጠያቂ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን አጀንዳ ለመፍጠርና የመንግሥት ፖሊሲ ላይ ግፊት ለማሳደር መጠቀም። ለምሳሌ በናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሲጨምር መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቡን ቀነስ አድርጎታል። ጋዜጠኞች እንዲህ ያሉ የመንግሥት ተግባራትን ከነባራዊ መረጃዎች ጋር ማናበብ አለባቸው። በእኛ ተቋም፣ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ብዛት በሚመለከት ያለውን መረጃ በመከታተል ዘገባዎች እየሠራንና የእንቅስቃሴ ገደቡ መላላቱ አግባብ ነው አይደለም የሚለውን ለማየት እየሞከርን ነው።

ምስል፤ ዓለማቀፍ የምርመራ አዘጋገብ ማእከል

በዛም ላይ፣ በናይጄሪያ ያሉ ጋዜጠኞች በጤና፣ ትምህርት እና መሠረተ ልማት ዙሪያ አጀንዳ ከመፍጠር ፈገድ በቂ መረጃዎችን እየተጠቀሙ ነው ብዬ አላስብም። በተቋማችን ልንሠራ የምንፈልገው አንዱም ዘገባ፣ በተለይ ከትምህርት ቤቶችና በትምህር ቤት ካሉ ሕጻናት ጋር በተገናኘ ያለውን የትምህርት መረጃ መመልከት ነው።

ትምህርት በሚቋረጥ ጊዜ መንግሥት ስለወደፊቱ ማሰብ እንዲጀምር ማስገደድ እንፈልጋለን። ይህንን መረጃም መንግሥት ተጨማረ ምን ያህል ትምህርት ቤቶች መገንባት እንዳለበት ለመተንበይ እንጠቀምበታለን። ምክንያቱም ልጆቻችን ትምህርት ቤት ሲመለሱ አካላዊ ርቀትን ማየት አለባቸው። ጋዜጠኞች እንዲህ ያሉ መረጃዎችን በተለይ ለአብዛኛው የምጣኔ ሀብት ጉዳይ አጀንዳ ለመፍጠር መጠቀም አለባቸው።

የፕሬስ ነጻነት ቀን በሚከበር ጊዜ፣ ወረርሽኙ በቁጥጥር ከዋለ በኋላ፣ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኀን ተቋማት እንዴት መቀጠል እንደሚችሉ ማሰብና መንገድ መፍጠር አለባቸው ብለሃል። ምን ዓይነት አዳዲስ መንገዶችን አስበሃል?

ጋዜጠኞች አዲስ፣ ወጪ ቆጣቢ የሆኑ የታሪክ መንገሪያ ወይም መዘገቢያ መንገዶች መጠቀምን መማር አለባቸው፣ በተለይ ቴክኖሊጂን። ነባራዊ የምርመራ ዘገባ ሥራዎች ወይም በጥቅሉ የትኛውም ዓይነት ጋዜጠኝነት፣ በቴክኖሎጂ የሚመራ ነው። እናም ጋዜጠኞች እንዲህ ያሉ የቴክኖሊጂ መሣሪያዎችን መጠቀም አለባቸው እንጂ በድሮና በባህላዊ ዘዴ ብቻ መጠቀም የለባቸውም። ለዚህ በየመንገዱ ምንጭ፣ መረጃና ሰነድ ፍለጋ ከመባዘን፣ ከእነዚህ አብዛኛውን በኢንርኔት ኦንላይን ሆነን ማግኘት እንደምንችል መረዳት አለብን።


ቤኖን ኸርበርት ኦሉካ፣ በዓለማቀፉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ ኤዲተር፣ በዩጋንዳ የመልቲሚድያ ጋዜጠኝ፣ በአገሩ የምርመራ ጋዜጠኝነት ማእከል ሆኖ የሚያገለግለው የ‹ዋችዶግ› መሥራቾች መካከል አንደኛው ሲሆን፣ በተጨማሪም የአፍሪካ የምርመራ ዘገባዎች ሕትመት ኅብረት አባል፤ 

Republish our articles for free, online or in print, under a Creative Commons license.

Republish this article


Material from GIJN’s website is generally available for republication under a Creative Commons Attribution-NonCommercial 4.0 International license. Images usually are published under a different license, so we advise you to use alternatives or contact us regarding permission. Here are our full terms for republication. You must credit the author, link to the original story, and name GIJN as the first publisher. For any queries or to send us a courtesy republication note, write to hello@gijn.org.

Read Next