በሰብ ሰሃራ አፍሪካ በሚገኙ በርካታ አገራት፣ አሁን ድረስ መረጃና የሕዝብ የሆኑ የመረጃ መዛግብትን ማግኘት ፈታኝና ከባድ ሥራ ነው። ለምን ቢባል ጋዜጠኞች መረጃ ሲጠይቁ የሚደግፋቸውና የመንግሥት ባለሥልጣናት የሕዝብ የሆኑ መረጃዎችን እንዲሰጡ ግድ የሚላቸው ሕግ አለመኖሩ ነው።
ሆኖም አንዳንድ አገራት ይህን ጽንፍ ቀይረው መረጃዎች በቀላሉ እንዲገኙ አስችለዋል። የመረጃ አቅርቦትና ተደራሽነትን በሚመለከት የሚመሩበት ሕግ ባለባቸው የሰብ ሰሃራ አፍሪካ አገራት፣ ለጋዜጠኞች የሚጠቅሙና ተመራጭ የሆኑ ምንጮች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
የአፍሪካ የመረጃ ነጻነት ማእከል፤ ብቸኛና ቀዳሚ የሆነ መላውን አፍሪካ የሚያዳርሱ የአኅጉሪቱ ምንጮች የሚገኙበት እንዲሁም መረጃዎቹን ተደራሽ ለማድረግ በተወሰነ ሕግ የሚመራ የመረጃ ምንጭ ነው። በአፍሪካም የመረጃ ነጻነት ሕጎች ዙሪያ መረጃዎችን ያቀርባል።
IFEX (ዓለማቀፍ ሐሳብን የመቀያየር ነጻነት) በአፍሪካ የመረጃ ነጻነት ሕጎች እንዲስፋፉ በማድረግ ጥሩ ሂደት ያሳለፈ ሲሆን፣ በትግበራም ያሉና የሚያጋጥሙ ችግሮችን የሚያካትት ነው።
ኬንያ፣ Reporting on Good Governance in Kenya.org የተባለ ድረ ገጽ የመረጃ ተደራሽነትን በሚመለከት ብሔራዊና የክልል ሕግና መመሪያዎችን ሲያብራራ፣ በጋዜጠኞች ልምድ ዙሪያ ዘገባዎችን ለንባብ ያቀርባል። ጥሩ የገጽ ቅንብርም አለው። እዚህ ላይ በካቲባ ኢንስቲትዩት በኬንያ ሕግ ዙሪያ የተዘጋጀ የመመሪያ መጽሐፍ መመልከት ይቻላል።
ላይቤሪያ፣ InfoLib የመረጃ ነጻነት ጥያቄዎችን ለማደራጀት የኦንላይን ዘዴዎችን ያቀርባል። ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ አገልግሎት ሰጪ ይሁን እንጂ፣ በላይቤሪያ የመረጃ ኮሚሽን ድረገጽ ‹ቴክ አክሽን› በሚል ማስፈንጠሪያ ስርም ይገኛል።
ሞዛምቢክ: Guia do Direito à Informação Para Jornalistas, በዓለማቀፍ ምርምርና ልውውጥ ቦርድ የተዘጋጀ፣ ለጋዜጠኞች የ2016 የመረጃ ነጻነት መመሪያ።
ናይጄሪያ፡ R2KNigeria ስለመረጃ ነጻነት ሕጎች ጠቃሚ መረጃዎችን ያቀርባል። የናይጄሪያው ኤክስትራክቲፍ ኢንዱስትሪ ግልጽነትን መነሻ በማድረግ በኢንተርኔት ለኦንላይን አገልግሎት ጥያቄዎች የመረጃ ነጻነት ሕጎችን ፖርታል አካትቷል። የፐብሊክ ሰርቪስ ሪፎርም ቢሮም በተመሳሳይ እነዚህን የመረጃ ነጻነት ሕች ያካተተ ፖርታል አለው። በሚያዝያ 2018 ደግሞ የማኅበረ ኢኮኖሚያዊ መብቶች እና ግዴታዎች ፕሮጀክት አንድ መመሪያ አሳትሟል። ይህም መረጃ የማግኘት መብትን በመጠቀም በጤና ዘርፍ፣ በትምህርት እንዲሁም በውሃ መስክ ያሉ ሙስናዎችን መጋፈጥ የሚል ነው።
ሩዋንዳ: Sobanukirwa ነጻ ገጽ ሲሆን፣ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በኢንግሊዝኛ፣ ኢንያሩዋንዳ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ያደራጃል።
ደቡብ አፍሪካ፡ ‹Open Democracy Advice Centre› የመረጃ ተደራሽነትን ከማስተዋወቅ አንጻር የመረጃ ሰነድ መጠየቂያ ፎርም ያቀርባል፣ ድጋፍም ያደርጋል። ‹Right2Know› የተባለውም በዋናነት ግልጽነትን በመደገፍ የሚሟገት ቡድን ነው።‹ ODAC› በተመሳሳይ የመረጃ ተደራሽነትን ከማስፋፋት አንጻር፣ መረጃ የማግኘት መብት ዙሪያ ድጋፍ ያደርጋል።
የደቡብ አፍሪካ የሚድያ ተቋም፡ በአፍሪካ የመረጃ ነጻነት ሕጎች ሊንክ የሚገኝበት ገጽ ያለው ነው፣
ዮጋንዳ: ‹መንግሥታችሁን ጠይቁ› ዩጋንዳ› (Ask your Gov Uganda) በኦንላይን በሚገኝ የመረጃ ነጻነት መጠየቂያ ፖርታል ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች በቀጥታ ለመንግሥት ተቋማት የመረጃ ጥያቄ የሚያቀርቡበት ነው። ድረ ገጹ በይፋ ለእነዛ ጥያቄዎች መልሶችን ይሰጣል።