Accessibility Settings

color options

monochrome muted color dark

reading tools

isolation ruler
» ጠቃሚ ምክር

ሃብት

Topics

በአፍሪካ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ፡ እርዳታ እና ድጋፎች

Read this article in

የምርመራ ዘገባ ሥራ ሁልጊዜም ውድ ነው። ዘርፉ በዓለም ደረጃ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ በገባበት በዚህ ጊዜ፣ በርካታ የሚባሉ የንግድ//ኮሜርሻል ሚድያዎች ግንዘብን እንደወትሮው ለምርመራ ዘገባ አይመድቡም።

ያንን ክፍተት ለመሙላት ጥቂት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋማት ጣልቃ ገብተዋል። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቼ የአገር ውስጥ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ዓለማቀፍ ነገር ግን አፍሪካን ማእከል ባደረገ መልኩ የምርመራ ጋዜጠኝነትን ለመደገፍ እርዳታዎችን ለመስጠት ያለሙ ናቸው።

የአፍሪካ የሚድያ ልኅቀት ማእከል (ACME)

በዩጋንዳ ካምፓላ የሚገኘው ይህ ማእከል፣ ለምርመራ ጋዜጠኝነት ሽልማት የሚሰጥበት ፕሮግራም አለው። እንዲሁም በአኅጉሪቱ በሙያው ብቁ ጋዜጠኞችን ለማፍራት ሥልጠናዎችን ይሰጣል። ዋና ግቡ መገናኛ ብዙኀን ወይም ሚድያ በኅብረተሰብ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃ የሚገኝበት፣ የባለሥልጣናትን ሥልጣን መቆጣጠር የሚያስችል መሣሪያ እንዲሆን እንዲሁም ሕዝባዊ ክርክር የሚደረግበት አሠራር የሚፈጥር፣ ውጤታማ መድረክ እንዲሆን ማድረግ ነው። ለሽልማት ፕሮግራሞቹ እንደ ‹ፎርድ ፋውንዴሽን›፣ ‹ረቨኑ ወች ኢንስቲትዩት›፣ ‹ፖፑሌሽን ሪፈረንስ ቢሮ› እና ‹ማክአርተር ፋውንዴሽን› የመሳሰሉ ዓለማቀፍ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋማትን አጋሮቹ አድርጓል።

የአፍሪካ ሚድያ ኢኒሽዬቲቭ (AMI)

የአፍሪካ ሚድያ ኢኒሺዬቲቭ በ2008 የተመሠረተው፣ በአፍሪካ ዴሞክራሲያዊ አመራር እና የኢኮኖሚ እድገት እንዲመጣ ትልቅ ሚና መጫወት ይችል ዘንድ ሚድያው እንዲጠናከር ነው። ይህን የሚያደርገውም ነጻነትን፣ ትብብርን፣ ብዝኀነትን እና የገንዘብ ማረጋጋት ኢኒሺዬቲቮችን በማበረታታት ነው። ቁልፍ ተግባራቱም በአፍሪካ ከሚድያ ባለቤቶችና አመራሮች ጋር አብሮ መሥራትና ለጋዜጠኝነት አሠራሮችና ፈተናዎች መልስ እንዲሰጡ አቅማቸውን ለማጠናከር ነው።

በተያያዘም ለጋዜጠኞች ሥልጠና እድሎችን መፍጠር፣ ለጥሩ ዘገባዎች ሽልማቶችን ማቅረብ፣ ለሚድያ ፖሊሲ ለውጦች ለውጥ እንዲኖር ቅስቀሳ ማድረግ፣ የሚድያ ጥናታዊ ምርምሮችን ማካሄድ እንዲሁም በትብብር ሐሳቦችን ማዳበር ላይ እገዛ ማድረግ ነው። ኢኒሺዬቲቩ የሚድያ ባለቤቶች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በወሳኝ ጉዳዮች የሚወያዩበት ዓመታዊ ስብሰባ የሆነው የአፍሪካ ሚድያ መሪዎች ፎረምን ያስተባብራል።

ዲደብሊው አካዴሚያ

ዲደብሊው አካዴሚያ የጀርመን ሕዝብ ዓለማቀፍ ብሮድካስተር የሆነው የዶቼ ቬለ ዓለማቀፍ ሚድያ ልማት አንድ ክፍል ነው። በአፍሪካም በ18 አገራት ባህላዊ ሚድያን፣ የኅብረተሰብ ሬድዮ ጣቢያዎችን እና ብሎገሮችን ይደግፋል። የዲደብሊው አካዴሚያ እንቅስቃሴዎች ትኩረታቸው ከፍተኛ ጥራትን ማጠናከር፣ ራስን የቻለ ሚድያ መሆንን እና ለሚድያ ባለሞያዎች ዘላቂ የሥልጠና ስርዓቶችም ጉልበት መስጠት ላይ ነው። የመናገር ነጻነትን እና የመረጃ ተደራሽነትን ለማሻሻል፣ ይልቁንም ለዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ ድጋፎችን ያደርጋል።

ፎጆ ሚድያ ተቋም

ፎጆ ሚድያ ተቋም መቀመጫውን በስዊድን ሊናዉስ ዩኒቨርሲቲ ያደረገ ነገር ግን በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚሠራ ተቋም ነው። ነጻ፣ በራሱ የሚመራና ሙያተኛ ጋዜጠኝነትን ለማጠናከር ከአገራዊና ክልላዊ አጋሮች ጋር ይሠራል። አዳዲስ ሚድያ ተቋማትን እና የሚድያ ድርጅቶችን እንዲሁም ጋዜጠኞችን በገንዘብና በፖለቲካ ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑም ፎጆ ይደግፋል። ዘላቂ የንግድ ሐሳቦችን በማዳበር እና የሌሎች የሚድያ የድጋፍ አገልግሎቶችን በማስተባበር ያግዛል። አሁን ላይ በአምስት የአፍሪካ አገሮች የሚሠራ ሲሆን፣ እነዚህም ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሩዋንዳ እና ዚምባቡዌ ናቸው። ነገር ግን ከእነዚህ አገራት ባሻገርም በተለያዩ አገራት ፕሮጀክቶችን ደግፏል፣ አካሂዷልም።

ፎርድ ፋውንዴሽን

የፎርድ ፋውንዴሽን ለትርፍ ያልተቋቋመ የአሜሪካ ትልቅ ፋውንዴሽን ሲሆን፣ በናይሮቢ፣ ሌጎስ እና ጆሐንስበርግ ቅርንጫፍ ቢሮዎች አሉት። መሪዎችን እና ተቋማትን ተጠያቂ የሚያደርግ የምርመራ ጋዜጠኝነትን፣ ዝም እንዲሉ ለተገደዱና ለተገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ድምጽ የሚሆን ዘገባንና በተቻለ መጠን ብዙዎችን ለማገናኘት ያለሙ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ይደግፋል። ፎርድ የማይደፈሩ የሚባሉ ፕሮፖዛሎችን እንዲሁም የድጋፍ ጊዜ ገደባቸው እየተጠናቀቀ የሚገኝ፣ በሂደት ላይ የሚገኙትን ይቀበላል። የሚሰጠው የድጋፍ መጠንም ከሃምሳ ሺሕ እስከ አንድ ነጥብ ሃያ አምስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል።

ሐይቮስ

ይህ የደች የልማት ተቋም ሲሆን፣ በዓለማቀፍ ደረጃም ይገኛል። ሐይቮስ የሴቶችን መብት እና የታዳሽ ኃይልን ጉዳይ ጨምሮ ከዓላማው ጋር የሚጣጣሙ ጉዳዮች ላይ ሥራዎችን ለሚሠሩ የሚድያ ተቋማት ድጋፎችን ይሰጣል። በተለየ አዲስ ሐሳብ ያላቸው የሚድያ ተቋማት እና ለዘለቀ ችግር አማራጭ መፍትሄዎችን የሚያመላክት ጋዜጠኝነት ላይ ያተኩራል። በኹለት ዋና ዋና ቅርንጫፎች የሚሠራ ሲሆን፣ እነዚህም በምሥራቅ አፍሪካ ኬንያ እንዲሁም ለደቡብ አፍሪካ ከዚምባቡዌ ሆኖ ነው። በደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ፣ ዩጋንዳ እና ማላዊም ብሔራዊ ቢሮዎች አሉት።

ዓለማቀፍ የሴቶች ሚድያ ፋውንዴሽን

መቀመጫውን በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የፋውንዴሽኑ ድጋፎች፣ በዋናነት የተዘጋጁት ለሴት ጋዜጠኞችና ፎቶግራፈሮች ነው። የደኅንነት ሥልጠናዎችን፣ የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ፣ የትምህርት ዕድሎችን እንዲሁም ድጋፎችን ያካትታሉ። ከዚህ ፋውንዴሽን የድጋፍ ኢኒሺዬቲቮች መካከል ለሴት ጋዜጠኞች ድጋፍ እና የድንገተኛ ጊዜ ድጋፍ የተሰኙት ይገኙበታል።

የሴት ጋዜጠኞች ድጋፍ የትምህርት እድሎችን፣ የምርመራ ዘገባዎችንና የሚድያ ልማት ኢኒሺዬቲቮችን የሚያግዝ ነው። የድንገተኛ ጊዜ ድጋፉ በሠሩት ዘገባ ምክንያት አደጋ ውስጥ ያሉ ሴቶችን ለማገዝ የሚውል ነው። ኹለቱም (የድጋፍ ዓይነቶች) በሂደት ላይ ያሉ ማመልከቻዎችን ይቀበላሉ።

አይሪሽ ኤይድ 

የአየርላንድ መንግሥት ይፋዊ የሆነ ዓለማቀፍ የልማት እርዳታ ፕሮግራም በዘጠኝ ‹ቁልፍ የሆኑ አጋር አገራት› ውስጥ ልማትን የሚያግዙ ፕሮጀክቶችን ያካሂዳል፣ ከእነዚህ አገራት ውስጥ ከአፍሪካ ውጪ ያለች አገር ቬትናም ብቻ ናት።

የተሻለ አመራር፣ ሰብአዊ መብት እና ተጠያቂነትን ለማጠናከር በሚያደርገው ጥረት፣ ለሚድያ ኤንጂኦዎች ድጋፍ ያቀርባል። በአፍሪካ ዋና አጋሮቹ ኢትዮጵያ፣ ማላዊ፣ ኬንያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሴራሊዮን፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛንያ እና ዛምቢያ ናቸው። በላይሪያ‹ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ዚምባቡዌም ይገኛል።

ሉሚኔት

የኦምዲያር ኔትወርክ ቅጥያ የሆነው፣ በጎ አድራጎት ላይ የሚሠራው ሉሚኔት፣ በ2018 ነበር የተመሠረተው። ሰዎች በአመራር፣ የሚፈልጉትን አገልግሎት ለማግኘት እና በሥልጣን ላይ ያለውን አካል ተጠያቂ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸውን የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት፣ በትርፍ እንደ ኢንቨስትመንት እንዲሁም ያለትርፍ ድጋፎችን ይሰጣል።

ከሚድያ እና ጋዜጠኝነት ጋር በተገናኘ፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ የሚድያ ተቋማትን እንዲሁም በጋዜጠኞች፣ የመረጃ ሳይንቲስቶች እና አክቲቪስቶች መካከል ያለውን ትብብር ለመደገፍ ይሞክራል። ያም ብቻ አይደለም፣ የአዲስ አባልነት ሞዴሎችን፣ የፕሬስ ነጻነትን ለማገዝ አዲስ መንገዶችን እንዲሁም የመረጃ ስህተቶችን ለመዋጋት ፈጠራ የታከለባቸው ጥረቶችንም እንደዛው።

ዋና መሥሪያ ቤቱ በለንደን የሚገኝ ሲሆን፣ በናይሮቢ ቢሮዎች አሉት። አሁን ላይ ትኩረቱን በሦስት ሰብ ሰሃራ አገራት፤ ማለትም በኬንያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ በሚሠሩ ድርጅቶች ላይ አድርጓል። ሆኖም ግን፣ ከእነዚህ ዋና ከተባሉ አገራት ውጪም ቢሆን አሳማኝ ፕሮጀክቶች ካሉ ለመደገፍ ፈቃደኛ ነው። የድጋፍ መጠኖችም ይለያያሉ።

የሚድያ ልማት ኢንቨስትመንት ፈንድ (MDIF)

የሚድያ ልማት ኢንቨስትመንት ፈንድ ያለትርፍ የኢንቨስትመንት ፈንዶችን የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህንን ድጋፍ የሚያደርገው ነጻና ራሳቸውን የቻሉ ሚድያዎች ስጋት ውስጥ በሆኑበት አገራት ለሚገኙ ራሳቸውን ለቻሉ ሚድያዎች ነው። ተቋሙ መጠነኛ ብድሮችንና አግባብ የሆኑ ኢንቨስትመንቶችን ቴክኒካል እገዛዎችን አካትቶ ያቀርባል። ይህን የሚያደርገውም ሰዎች ነጻና ስኬታማ ማኅበረሰብ እንዲፈጥሩ የሚያስችላቸውን ዜና፣ መረጃ እንዲሁም የክርክር መድረክ ለሚፈጥሩ ሚድያዎች ነው። ተልዕኳቸው ራሳቸውን የቻሉ የዜና ኩባንያዎች፣ ለወደፊታቸው ኢንቨስት እንዲያደርጉ እና ተወዳዳሪና ተለዋዋጭ ቢዝነስ እንዲፈጥሩ ለማስቻል በገንዘብ ማጠናከር ነው።

የምዕራብ አፍሪካ ሚድያ ፋውንዴሽን (MFWA)

ይህ ፋውንዴሽን የሚድያ ልማት ኤንጂኦ ሲሆን፣ በ16 የምዕራብ አፍሪካ አገራት ይንቀሳቀሳል። የንግግር ነጻነት ፕሮግራም ያለው ሲሆን፣ በተጨማሪም መደበኛ የሥልጠና እድሎችን የሚሰጡ እንዲሁም በተለያዩ ድጋፎች የምርመራ ጋዜጠኝነትን የሚያግዙ የሚድያ እና የመልካም አመራር ኢኒሺዬቲቮች አሉት። በ2018 በምዕራብ አፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኞች ኔትወርክን ከፍቷል። እንዲሁም ዓመታዊውን የምዕራብ አፍሪካ የሚድያ ልኅቀት ኮንፈረንስ እና ሽልማት ያስተባብራል።

የደቡብ አፍሪካ የሚድያ ተቋም (MISA)

በ1992 የተመሠረተው የደቡብ አፍሪካ የሚድያ ተቋም፣ በደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ የሚገኙ አስራ አንድ ብሔራዊ ቅርንጫፎችን በስሩ የያዘ ነው። መቀመጫው በናሚብያ ዊንድሆክ ነው። የተቋሙ እንቅስቃሴዎች የሚያተኩሩት ነጻ፣ ራሱን የቻለና ብዝኀነትን የሚያስተናግድ ሚድያን በአካባቢው ማጠናከር ላይ ነው።

ይህንንም የሚያደርጉት በመቀስቀስ፣ ለሚድያ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ በመስጠት፣ የሚድያ ነጻነትን በመከታተል፣ ለንግግር ነጻነትና ለመረጃ መብት በመሟገት እንዲሁም የሕግ ድጋፍ በመስጠት ነው።በእያንዳንዱ ብሔራዊ ቅርንጫፍ፣ የፕሮግራም ትግበራዎች በፖለቲካ ሁኔታ እና በየአገሩ ካለው ፍላጎት አንጻር የሚወሰኑ በመሆናቸው፣ እንቅስቃሴዎች ይለያያሉ።

የዋና ድርጅቶች ድረገጽ ትንታኔዎችን፣ ሕጎችና ዘገባዎችን አጣምሮ የያዘ የምንጭ ማእከል አለው። የደቡ አፍሪካ የሚድያ ተቋም ቅርንጫፎቹ በቦትስዋና፣ ማላዊ፣ ዛምቢያ እና ዚምባቡዌ የሚገኙ ሲሆን፣ የጭብጥ ጉዳዮች ላይ ልኅቀትን በማጠናከር የብሔራዊ ሚድያ ሽልማት አለው።

የገንዘብ ክትትል ድጋፎች

የገንዘብ ክትትል ድጋፍ እድሎች በJournalismfund.eu የሚቀርቡ ናቸው። አጋሮችም የታሰቡት የአፍሪካ፣ የእስያ እና የአውሮፓ ጋዜጠኞች ድንበር ተሻጋሪ ሕገወጥ የገንዘብ እንቅስቃሴዎችን፣ የግብር ብዝበዛዎች እና በአፍሪካ፣ እስያና አውሮፓ ሙስናዎችን ለሚመረምሩ ለተጣመሩ ቡድኖች ነው።

Journalismfund.eu በተጨማሪ ቢያንስ ከኹለት አገር ለተውጣጡ የጋዜጠኛ ቡድኖች፣ በአፍሪካ እና በእስያ መካከል የአገራት ድንበር ተሻጋሪ ትብብሮችን ይቀበላሉ። በ2020 ሦስት ማመልከቻ ዙሮች ያሉ ሲሆን፣ የእነዚህ ማብቂያ ቀንም መጋቢት 7፣ ሠኔ 8 እና ጳጉሜ 4 ነው።

ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽኖች

ኦፕን ሲሳይቲ ፋውንዴሽኖች በዓለማቀፍ ደረጃ የሚድያ ፕሮጀክቶችን ከሚደግፉ ግዙፍ የግል ድጋፍ ሰጪዎች መካከል ናቸው። በለንደን ያለው የአፍሪካ ቢሮአቸው፣ በአፍሪካ አራት አገራት ክልላዊ እና ብሔራዊ ቢሮዎች በቅርበት ይሠራል። በክልል ደረጃ ፕሮጀክታቸው ፋውንዴሽኑ ቅድሚያ ከሚሰጠው ጉዳይ ጋር የተሰናሰለ የሚድያ ተቋማትን፣ ኅብረቶችን፣ ቅንጅቶችን እና ጋዜጠኞችን ይደግፋሉ።

ማእከላዊ የሆነ የማመልከቻ ሂደት የለም፣ ነገር ግን የድርጅቱ የክልል ፕሮግራሞች መደበኛ የማመልከቻ ጥሪዎችን ያደርጋሉ። በዚህም በምሥራቅ አፍሪካ የኦፕን ሶሳይቲ ኢኒሺዬቲቭበምዕራፍ አፍሪካ የኦፕን ሶሳይቲ ኢኒሺዬቲቭበደቡብ አፍሪካ የኦፕን ሶሳይቲ ኢኒሺዬቲቭ እና የደቡብ አፍሪካ የኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንን ያጠቃልላሉ።

የፑሊትዘር ማእከል

የፑሊትዘር ማእከል <Persephone Miel fellowships› ከአሜሪካ ውጪ ላሉ፣ በአሜሪካ ለሚገኙ የኢንግሊዘኛ ሚድያዎች ከቤታቸው ሆነው መዘገብ ለሚፈልጉ ጋዜጠኞችም ክፍት ናቸው። ይህ ፌሎሺፕ፣ እንደ ፔርሴፎን ገለጻ፣ ብልሃት የሚፈልጉ ጉዳዮችን የሚመረምሩና የግለሰብ ጋዜጠኞች ነጠላ ዘገባ ሳይሆን በጣም ወሳኝ የሆነ ጥናት ያቀረቡ የጋዜጠኝነት ፕሮጀክቶችን ይደግፋል።

በተጨማሪም የማእከሉ የሬይንፎረስት የጋዜጠኝነት የገንዘብ ድጋፍ በላቲን አሜሪካ፣ አፍሪካ እና እስያ ሞቃታማና ዝናባማ ደኖች ዙሪያ ለሚሠሩ ዘገባዎች ትብብር ያደርጋል። በ2019 ይኸው ድጋፍ በአካባቢያዊና ክልላዊ ማሰራጫዎች ከሚዘግቡ የአፍሪካ ጋዜጠኞች የሚነሱ ፕሮፖዛሎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት ጀመረ።

የስዊስ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ

ከግሎባል ሳውዝ ጋር እንደ አንድ የልማት ትብብር አካል፣ የስዊዘርላንድ ዓለማቀፍ ልማት ኤጀንሲ፣ በጤና እና ሥልጠና፣ ሥራ እና የገቢ ፈጠራ፣ የገጠር ልማት፣ የአገር ግንባታ እና የአመራር ለውጦች ዙሪያ ከ800 በላይ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞችን ያካሂዳል። የሚሠራውም የሕግ የበላይነት፣ ሰብአዊ መብት እና ፍትህን ለማጠናከር የሚሠራ ሲሆን፣ ይህም ዘላቂ የድህነት ቅነሳ እና ልማትን መደገፍን ታሳቢ ያደረገ ነው። በታንዛንያም የምርመራ ጋዜጠኝነትን በመደገፍ የሚያካሂደው ፕሮግራም አለ።

ታኮ ኪዩፐር› ግራንትስ

እነዚህ ድጋፎች በደቡብ አፍሪካ የህትመት ሚድያ የምርመራ ጋዜጠኝነትን ለማበረታታት የሚደረጉ ናቸው። በዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል ለሚተዳደሩ ናቸው። በዚህም ለደቡብ አፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኞች በዓመት 350 ሺሕ ዛር ወይም 23 ሺሕ ዶላር ይሰጣል። ድጋፍ ሰጪዎቹ በፕሮፖዛል ላይ በአሳማኝ ሁኔታ የቀረበ ከሆነ ማንኛውንም ያህል ገንዘብ መስጠትን ከግምት ያስገባሉ። ሆኖም የሚቀበሉት፣ የመጽሐፍፕሮጀክቶችን ጨምሮ፣ ደቡብ አፍሪካ ላይ በየጊዜው ተጽእኖ የሚያደርጉ ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚቃኙ፣ ሰፊና ጥልቀት ያላቸው የዘገባ ፕሮጀክቶችን ብቻ ነው።

ዊትስ አፍሪካ-ቻይና የዘገባ ፕሮጀክት

የአፍሪካ-ቻይና የዘገባ ፕሮጀክት በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ በሚገኘው ዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል የሚዘጋጅ ነው። ዓላማውም ለጋዜጠኞች የአቅም ግንባታ እድሎችን በማቅረብ፣ በአፍሪካ-ቻይና ጉዳዮች ላይ ያሉ ዘገባዎችን ጥራት ማሳደግ ነው። ይህ ፕሮጀክት የዘገባ ድጋፎችን ሲያደርግ የሥልጠና ወርክሾፖችና ለአፍሪካ እና ለቻይና ጋዜጠኞች የተወሳሰቡ ጉዳዮችንና ያልተነገሩ ታሪኮችን እንደሚመረምሩ ሌሎች እድሎችን ፈንድ ያደርጋል። ዓመቱን ሙሉ የሚደረገው ድጋፍ ከሦስት መቶ እስከ ሦስት ሺሕ ዶላር የሚደርስ ነው።

Republish our articles for free, online or in print, under a Creative Commons license.

Republish this article


Material from GIJN’s website is generally available for republication under a Creative Commons Attribution-NonCommercial 4.0 International license. Images usually are published under a different license, so we advise you to use alternatives or contact us regarding permission. Here are our full terms for republication. You must credit the author, link to the original story, and name GIJN as the first publisher. For any queries or to send us a courtesy republication note, write to hello@gijn.org.

Read Next

የናይጄሪያው ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) በኮቪድ 19 ምላሽ ተጠሪነትን ለመፍጠር እያደረገ ያለው ግፊት

መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።