ሃብት ጠቃሚ ምክር
የምርመራ ጋዜጠኝነት መመሪያዎች
ጠቃሚ ነጥቦች፣ መሣሪያዎችና ተጨማሪ ሥልጠናዎችን እየፈለጉ ነው? ከታች የሚታዩት መመሪያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ ተጨባጭ ጥናቶችን እና ምሳሌዎችን ያቀርባሉ። አብዛኞቹ በነጻ የሚገኙ ናቸው፣ ክፍያ አላቸው ተብለው ከተጠቀሱት ውጪ።
ጠቃሚ ነጥቦች፣ መሣሪያዎችና ተጨማሪ ሥልጠናዎችን እየፈለጉ ነው? ከታች የሚታዩት መመሪያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ ተጨባጭ ጥናቶችን እና ምሳሌዎችን ያቀርባሉ። አብዛኞቹ በነጻ የሚገኙ ናቸው፣ ክፍያ አላቸው ተብለው ከተጠቀሱት ውጪ።
በቢቢሲ ቁጥር አንድ በሚለው የኦንላይን መርማሪው ፖል ማየርስ የቀረበው ኦንላይን የጥናት መሣሪያዎችና የምርመራ ዘዴዎች ለዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ አንባቢዎች የኦንላይን የጥናት ፍለጋዎች መነሻ ሆኖ አገልግሏል። ይህ የእርሱ ‹ሪሰርች ክሊኒክ› የተባለ ድረገጽ፣ የብዙ ጥናታዊ ሥራዎች ሊንክ እና የ‹ጥናት ግብዓቶች› ይገኙበታል። ማየርስ በ2019 የኔትወርኩ ዌብናር ላይ ሰዎችን ኦንላይን እንዴት እናገኛለን ለሚለው ጠቃሚ ምክሮችን አቅርቧል። የዓለማቀፉ ኔትወርክ ማየርስን […]
በሰብ ሰሃራ አፍሪካ በሚገኙ በርካታ አገራት፣ አሁን ድረስ መረጃና የሕዝብ የሆኑ የመረጃ መዛግብትን ማግኘት ፈታኝና ከባድ ሥራ ነው። ለምን ቢባል ጋዜጠኞች መረጃ ሲጠይቁ የሚደግፋቸውና የመንግሥት ባለሥልጣናት የሕዝብ የሆኑ መረጃዎችን እንዲሰጡ ግድ የሚላቸው ሕግ አለመኖሩ ነው።
መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።
በተፈጥሮው፣ የምርመራ ጋዜጠኝነት አደገኛ ሲሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ዘጋቢዎችና ኤዲሪተሮችን ስጋት ላይ ይጥላል። ሙሰኛ የሆኑና እጃቸው የዘረመ የመንግሥት ባለሥልጣናት ቆሻሻ የሚያወጡ ጋዜጠኞች ማስፈራሪያዎ ይገጥሟቸዋል። ይህም የምርመራ ሥራውን ለማስቆም የሚድያ ተቋማቸውን እስከመጨረሻው ዝም እስከማሰኘት የሚደርስ ጥረት ነው። እነዚህን ጋዜጠኞች ከደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት ለመጠበቅ፣ አንዳንድ የአፍሪካ እና ዓለማቀፍ ድርጅቶች፣ በተመረጡ የአፍሪካ አገራትም ሆነ በመላው አኅጉሪቱ፣ ችግር ላይ ላሉ ምስጢር አጋላጭ ጋዜጠኞች ድጋፍ የሚያቀርቡበትን ፕሮግራም ሠርተዋል።
የምርመራ ዘገባ ሥራ ሁልጊዜም ውድ ነው። ዘርፉ በዓለም ደረጃ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ በገባበት በዚህ ጊዜ፣ በርካታ የሚባሉ የንግድ//ኮሜርሻል ሚድያዎች ግንዘብን እንደወትሮው ለምርመራ ዘገባ አይመድቡም።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ በኮቪድ 19 ዙሪያ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በሚመለከት ለኅብረቱ ንግግር ሲያደርጉ፤