Accessibility Settings

color options

monochrome muted color dark

reading tools

isolation ruler

ሪፖርት ማድረግ

Topics

በአፍሪካ የኮቪድ 19 ዘገባ፤ ግብዓት የሚሆኑ ነጥቦች

Read this article in

ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ እና የመድኃኒት ካርታ

ኮቪድ 19ን የተመለከቱ ጉዳዮችን ለመዘገብ ጥሩ የሚባለው መንገድ የትኛው ነው? መጀመሪያ አንድ አንጻር መምረጥ ያስፈልጋል። የትኛውንም ርዕሰ ጉዳይ ቢያነሱ፣ ወረርሽኙ ሁሉም በሚባል ደረጃ ዘገባዎች ውስጥ አካል እየሆነ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ፣ በካምፓላ የሚገኘው በአፍሪካ የሚድያ የልኅቀት ማእከል (African Centre for Media Excellence) ተከታዩን ዝርዝር በየዘርፉ አዘጋጅቷል። ይህም ከግብርና እና ምግብ ተነስቶ ምጣኔ ሀብት፣ ትምህርት፣ ሃያማኖት፣ ስፖርት እንዲሁም ጥበብና መዝናኛን ምድቦችን የሚያካትት ነው።

ምድቦቹ የሚከተሉት ናቸው፤

ግብርና እና ምግብ 

 • የዓለም ዐቀፍ የምግብ ዋጋ መውረድ የአገራችሁን ነጋዴዎች እንዴት ተጽእኖ አደረጋባቸው? የትኞቹስ ሸቀጦች የበለጠ ተጎድተዋል? ይህስ የገጠሩን ገበያ ድረስ ወርዷል?
 • በወረርሽኙ ምክንያት በአገራችን ያለው ወይም ተጠብቆ የነበረው የምግብ ቀውስ እንዴት ተባባሰ?
 • መደበኛ ባልሆነ የግብርና ዘርፍ በሚሠሩ ተጋላጭ ማኅበረሰቦች ላይ ወረርሽኙ ያደረሰው ተጽእኖ ምንድን ነው?
 • በትምህርት ቤት ምገባ ላይ ጥገኛ የነበሩ ልጆችና የቤተሰባቸውን የምግብ ሁኔታ በሚመለከት ያሉ ስጋቶችን ለመቆጣጠርምን ዓይነት ፕሮግራሞች በተግባር ላይ ውለዋል? እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላትስ ምን ዓይነት ሰብአዊ ድጋፎች አሉ?
 • በምግብ ማምረትና የእንስሳ እርባታ ላይ የተሰማሩና በዛም ላይ ጥገኛ የሆኑ ቤተሰቦች የተፈጠረውን የግብርና ግብዓት ሰንሰለት መዛባት እንዲሁም የእንስሳ ገበያ ለማግኘት እድል አለመኖሩን እንዴት እየተቋቋሙት ነው?
 • ከፊልና ሙሉ አርብቶ አደሮች በድንበር መዘጋት ተጽእኖ አድርጎባቸዋል? የቀንድ ከብት እንቅስቃሴ እንዳይገደብና እንዳይስታጎል ለማድረግ መንግሥት ወይም ከእነዚህ ማኅበረሰቦች ጋር የሚሠሩ የየአካባቢው ባለሥልጣናት ምን እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው?
 • በአገራችሁ በኮቪድ 19 ምክንያት የምግድ ደኅንነት እርምጃዎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ከሚገባው ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ይዟል? የምግብ እጦትን ለመከላከል በመንግሥት፣ ሲቪል ማኅበራት እና ማኅበረሰብ በኩል ምን ዓይነት የፖሊሲ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው?
 • በወረርሽኙ ምክንያት የእነማን የምግብ ዋስትና እና የኑሮ ሁኔታ ነው የበለጠ ለአደጋ የተጋለጠው?
 • በቤት ውስጥ መቀመጥ ግድ በተባለበት ጊዜ ቋሚ የሰብል ምግቦች እንዲሁም ጤናማ ምግቦች ሽያጭ እና አቅርቦትን ለማረጋገጥ ምን ተሠርቷል?
 • ሰዓት እላፊ፣ የእንቅስቃሴ ገደብ እና የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫዎች መታገድ አባወር አርሶና አርብቶ አደሮችን ላይ እንዴት ተጽእኖ አደረገ?
 • በአንበጣ መንጋ ወረራ፣ ያልተጠበቀ ዝናብና ጎርፍ ምክንያት የተጎዱ አርሶ አደሮች ባሉባቸው ማኅበረሰቦች ወረርሽኙ ተጋላጭነታቸውን ምን ያህል ጨምሯል? እነዚህን ማኅበረሰቦች ድጋሚ ለማቋቋም ምን ዓይነት ድኅረ ወረርሽኝ ጥረቶች ታቅደዋል?
 • በከተማ እንዲሁም በገጠር ለየትኞቹ የማይበለሹ ዕቃዎች ነው ፍላጎት እየጨመረ ያለው? ሳይበለሹ መቆየት ለሚችሉ እንደ ስንዴ፣ ማሽላ፣ የካሳቫ ዱቄት፣ ባቄላ፣ አተር፣ ለውዝ ያሉ የምግብ ዓይነቶች ዋጋስ ጨምሯል? አቅራቢዎችስ እየጨመረ ከመጣው ፍላጎት ጋር በእኩል መራመድ ችለዋል?
 • ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለመመገብ በአገራችሁ ምን ዓይነት የድንገተኛ ጊዜ የምግብ ስርጭት ስርዓት ተዘርግቷል? እነዚህ ስርዓቶች ምንድን ናቸው? ማን ነው እየመራቸው ያለው? እንዲሁም ለታለመላቸው ዓላማ እየዋሉ ነው ወይ? በእነዚህ የማረጋጋት ጥረቶች ላይ የምግብ አከፋፋዮች እንዲሳተፉ ምን ዓይነት እድሎች ወይም አጋጣሚዎች አሉ? የምግብ አቅርቦት ማረጋጋትን ተደራሽ ለማድረግ ያለው ፈተና ምንድን ነው?
 • ኮቪድን ለመከላከል የተደረጉ እርምጃዎች የእህል ዘር፣ የእንስሳት መድኃኒት፣ የማዳበሪያ፣ እና ጸረ ተባይ አረም ስርጭት ላይ እንዴት ተጽእኖ አደረገ? የአገር ውስጥ እንዲሁም ዓለማቀፍ የግብርና ግብዓት አቅራቢዎች በአቅርቦት ስርዓታቸው ያለውን መስጓጎል ለመቀነስ ምን እያደረጉ ነው?
 • የግብርና ውጤቶችን ለማስገባት እንዲሁም ለማስወጣት የከለከለው የድንበር መዘጋጋት ከፍተኛ እንዲሁም አነስተኛ እርሻ ባለቤት የሆኑ ነጋዴዎች ላይ ምን ያስከትላል? በዚህስ የግብርና ምርት ውጤቶች ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ተደርጓል?

ምጣኔ ሀብትና ገንዘብ

 • በዓለም ዐቀፍ ግብይት ውስጥ ያሉ እንደ ነዳጅ፣ ጋዝ የተለያዩ ማእድናት እንዲሁም ምግብ የመሳሰሉ ዕቃዎችና ሸቀጦች ዋጋ መቀነስ የአገራችሁ ምጣኔ ሀብት ላይ እንዴት ተጽእኖ አሳደረ? እንዲህ ካሉ የዋጋ አለመረጋጋቶች አገራችሁን ለመጠበቅ ምን እየተሠራ ነው?
 • ኮቪድ 19 ያስከተለውን ምጣኔ ሀብታዊ ፈተና ለመፍታት አገራችሁ በክልላዊ እንዲሁም በአኅጉራዊ እንቅስቃሴዎች/ተግባራት ላይ እንዴት እየተሳተፈች ነው?
 • የኮቪድ 19ን ምጣኔ ሀብታዊ እንዲሁም የገንዘብ ተጽእኖ ለመፍታት የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ያለው ማን ነው?
 • ፓርላማዎች የድጋፍ በጀት ማጽደቃቸውን እንዲሁም መንግሥት አዲስ የገንዘብ ምደባ ተግባራዊ ከማድረጉ አንጻር፣ ገንዘቡ በምን መንገድ አገልግሎት ላይ እየዋለ እንደሆነ በግልጽት እየተገለጸ ነው ወይ? እነዚህን የገንዘበ ፈሰሶችን በመምራት ኃላፊነት ላይ ያለው ማን ነው? የሕዝብን ሀብት ከመጠቀም አንጻር ግልጽነትና ተጠያቂነት ይስተዋላል ወይ?
 • የምጣኔ ሀብት መቀዛቀዙን ተከትሎ በአገራችሁ የገንዘብ ፖሊሲ ተቀይሯል? ምን ዓይነት የገንዘብ ፖሊሲስ ከግምት ውስጥ ገብቷል?
 • በአገራችሁ የምጣኔ ሀብት ድቀት እንዲሁም ሲከፋ ምጣኔ ሀብታዊ ዝቅጠትን/ቀውስ ለመከላከል ምን እየተሠራ ነው?
 • በእንቅስቃሴ ገደቡ ጊዜ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፈተና ምንድን ነው?
 • ከኢንተርኔት ዓለም መስመር ውጪ ይሠሩ የነበሩ ንግድ ሥራዎች አገልግሎታቸውን አስተካክለው ሥራቸውን ወደ በኢንተርኔት መስመር ለመቀየር የእንቅስቃሴ ገደብና መዘጋጋቱን እንዴት እየተጠቀሙበት ነው? የንግድ ሥራዎችን በኢንተርኔት መስመር ለማካሄድ ቀጣሪዎችስ ሥልጠና እየሰጡ ነው? ምን ዓይነት ቢዝነሶች ናቸው ይህ እየተገበሩ ያሉትስ? የንግድ ሥራን ወደ ኢንተርኔት መስመር ለማዘዋወር የሚያስፈልጉት እንዲሁም ፈተና የሚሆኑትስ ምንድን ናቸው?
 • በአገራችሁ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምን ዓይነት የንግድ ሥራ እድሎችን ፈጥሯል? እንዴትስ እየተሠራበት ነው? ማንስ ነው በሚገባ እየሠራበት ያለው?
 • የእንቅስቃሴ ገደቡ በአምራቾች ላይ ምን ተጽእኖ አሳደረ? የአቅርቦት መዛባት የአገር ውስጥ እንዲሁም የውጪ ምርት የሆኑ እቃዎች እንዳይገኙ መቀነስን አስከትሏል ወይ? በአምራች ዘርፍ ይህ መዘጋጋት ያስከተለው ወጪ ምንድን ነው?
 • ለቢዝነስ ማኅበረሰቡ የግብር ስርዓት ለማሻሻል መንግሥትና የገቢዎች ባለሥልጣን ምን ዓይነት እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርገዋል?
 • የማእድን ቁፋሮና የነዳጅ ዘርፉ በንግድ እንቅስቃሴ መዳከም ምክንያት እንዴት ዓይነት ተጽእኖ አርፎባቸዋል? በገዢ እጥረትስ የትኞቹ አገራት በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል? በሸቀጦች ዋጋ መቀነስስ የማዕድን ቁፋሮ እና ነዳጅ ሥራዎች ተጎድተዋል?
 • በእጅ መታጠብ ንቅናቄ ምክንያት የውሃ እና የኤሌክትሪክ ፍላጎት ላይ ጭማሪ ነበር? የእነዚህ መገልገያዎች አቅራቢ ኩባንያዎች እየጨመረ ያለውን ፍላጎት ወይም የሕዝቡን የዋጋ ይቀነስልን አቤቱታ እንዴት አስተናገዱ?
 • የአፍሪካ የአኅጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና ተግባራዊ ይሆናል የተባለው ጁላይ 2020 ላይ ነበር። ለአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው አኅጉራዊ የንግድ ትስስር ምክክር በኮቪድ 19 እንዴት ተጽእኖ ደረሰበት? ከወረርሽኙ በኋላስ በአኅጉሪቱ የምጣኔ ሀብት ለማሻሻልና ኢንቨስትመንትን ከፍ ለማድረግ ምን ተስፋዎች አሉ?
 • ንግድ ተቋማትና ግለሰቦች ኮቪድ 19 ለሚያሳድረው ተጽዕኖ ኢንሹራንስ አላቸው ወይ? ኮቪድ 19 አዲስ በሽታ ሲሆን በነባር የኢንሹራንስ ስምምነት ዝርዝር ውስጥ የለም። ነገር ግን ለንግድ ሥራ መስተጓጎል፣ ለምርት እጦት እንዲሁም ለሞት ተብሎ የተቀመጠ አማራጭ የኢንሹራንስ ዓይነት አለ? የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለዚህ ጉዳይ ምን ዓይነት ምላሽ እየሰጡ ነው?

ትምህርት

 • አገራዊ የሆኑ ፈተናዎችንና ግምገማዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ለማስተናገድ የአገራችሁ እቅድ ምንድን ነው? ለፈተና እንዲሁም ግምገማዎችን ለማካሄድስ ምን ዓይነት አዳዲስ መንገዶች ከግምት ውስጥ ገብተዋል?
 • በመንግሥት፣ በትምህርት ቤቶች እንዲሁም መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ይቀርቡ የነበሩ ነጻ የትምህርት ግብዓቶች አሁን ላይ እንዴት እያገለገሉ ነው፣ በምን መንገድስ ተይዘዋል? እነዚህን ሀብቶች በመጠቀምና ተደራሽ በማድረግስ ምን የገጠሙ ፈተናዎች አሉ?
 • በርቀት ያሉ ተማሪዎችን ለመደገፍ የመንግሥት እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች ምን እያደረጉ ነው፣ ምንስ እያደረጉ አይደለም?
 • ልጆችን በቤት ለማስተማር በቂ እውቀት እንዲሁም አቅም የሌላቸው ወላጆች ምን ዓይነት ፈተናዎች ገጥሟቸዋል? ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ትምህርት ቤቶች ወይም ሲቪል ማኅበረሰቦች የተገኘ ድጋፍስ አለ?
 • ተማሪዎች የትምህርት ቤቶች የተዘጋጉበትን ወቅት እንዴት እያሳለፉት ነው?
 • መምህራን፣ ወላጆች እንዲሁም የትምህርት ቤት ሠራተኞችን ለመደገፍ የትኞቹ ማኅበረሰቦች በመስመር ላይ ይገኛሉ? ምን ዓይነት መረጃዎችስ ናቸው በእነዚህ ማኅበረሰቦች እየተንሸራሸሩ ያሉትና እንዴትስ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው?
 • የመማር ችግር ላለባቸው ወላጆችስ ምን ዓይነት መሣሪያዎች ይገኛሉ?
 • ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የርቀት ትምህርት አማራጭን እንዴት እየተጠቀሙ ነው? የርቀት ትምህርትን በመተግበር ምን ዓይነት ፈተናዎች ገጥመዋል፣ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆችስ የተማሪዎችና የሠራተኞቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት ምን ዓይነት ምላሽ እየሰጡ ነው?
 • የትምህርት ቤት ድጋፍ ያገኙ የነበሩ ሠራተኞች ዕጣ ፋንታ ምንድን ነው? አሁንም ደሞዝ እያገኙ ነው ወይ? ከመንግሥት ውጪም ከትምህርት ቤት አመራሮች ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ አግኝተዋል ወይ?

አመራር

 • በአገራችሁ ባለው የኮቪድ 19 መከላከል እቅድ ውስጥ በታሪክ የተገለሉ የሚባሉ ወይም በቂ ውክልና የሌላቸው ቡድኖች ተካተዋል ወይ? ይህስ እንዴት ተግባራዊ እየሆነ ነው? የጎደለስ አለ? ቸል እየተባለ ያለው ማን ነው?
 • የኮሮና ቫይረስ በቤት የመቀመጥ ምላሽን በማገዝ በኩል፣ የሰብአዊ እንዲሁም የገንዘብ እርዳታ አመራርን እየተከታተለ ያለው ማን ነው? እነዚህን ድጋፎች በመጠቀም በኩል መንግሥት ግልጽነትን ለማረጋገጥ ምን እያደረገ ነው? ድጋፉ አብዩዝን ሊያፍፍሙ የሚችሉ የተጠያቂነት ሉፕሆሎች የትኞቹ ናቸው?
 • የእንቅስቃሴ ገደቡ ትምህርት፣ ሥራን እንዲሁም መረጃዎችን ወደ ኦንላይን ካዘዋወረው፣ በአገራችሁ ያለውን የዲጂታል ተደራሽነት ልዩነት አድሬስ ለማድረግ ምን እየተሠራ ነው? የኢንተርኔት ተደራሽነትን አና አፎርደቢሊቲን በሚመለከት ያሉ ምክክሮች ምንድን ናቸው? የግሉ ዘርፍ እንዲሁም መንግሥት ለዚህ ጉዳይ እንዴት ምላሽ እየሰጡ ነው?
 • ‹በቤት ቆዩ› ወይም ‹ባላችሁበት ሁኑ› የሚለው መመሪያ የፍርድ ቤት ሂደቶች ላይ እንዴት ተጽእኖ አደረገ? የፍርድ ቤት ትዕዛዞች ተፈጻሚነትንስ ከፊል እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ መዘጋጋቱ እንዴት ተጽዕኖ አሳድሮበታል?
 • የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች መታገዳቸው ተጋላጭ ለሆኑና ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድና ለመምጣት ይህን አገልግሎት መጠቀም የሚያስፈልጋቸው ደሃ የማኅበረሰብ ክፍሎች ምን ተጽእኖ አሳደረ?
 • በዚህ ወቅት አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነት ያለባቸው የሕግ አስፈጻሚ ኃላፊዎች፣ የመንግሥት ሰዎችና የፖለቲካ ተሿሚዎች ዙሪያ ሙስናን ለማስቆም ምን እየተሠራ ነው? በቤት ውስጥ በመቀመጥ እርምጃ ተግባራዊነት አመራር ላይ ሙስና ካለ፣ ይህ ሙስና ምን ዓይነት መልክ አለው? ከዚህ በስተጀርባስ ማን አለ?
 • በወረርሽኙ ምክንያቱ የትኞቹ ቁልፍ የመንግሥት እንቅስቃሴዎች ተራዝመዋል ወይም ተጀምረው ተቋርጠዋል? ይህስ እንደ ሕግ ማውጣት፣ የሕዝብ ቆጠራ እንዲሁም ምርጫ ያሉ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ እንዴት ተጽእኖ አድርጓል?
 • ከከተማ በርቀት ላይ ያሉ ማኅበረሰቦች የኮቪድ 19 መረጃዎችን እንዴት እያገኙ ነው? መንግሥትስ መረጃን ለሁሉም ተደራሽ መሆኑን ለማረጋገጥ ምን እያደረገ ነው?
 • ኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመንግሥትን ግልጽነት ላይ እንዴት ተጽእኖ አደረገ? የመረጃ ልውውጥ ፍሰትን ጨምሮታል ወይስ ተጠያቂነትን ቀንሷል? በዚህ ምክንያትስ ዜጎች ለመንግሥትና ለተመረጡ መሪዎች ያላቸው ዕይታ እንዴት ተቀይሯል?
 • የየአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት በአካባቢያቸው አዳዲስና የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የኅብረተሰብ ጤና መመሪያዎችን እንዴት ለተግባር እያዘጋጁ ነው?
 • ያለ ኢንተርኔት አማራጭ የመንግሥት ቢሮዎች እንዴት ነው ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉት? በአገልግሎት ላይ መስተጓጎል ገጥሞስ ያውቃል፣ ይህስ ምን ተጽእኖ አድርጓል?
 • የፍትህ ስርዓቱ ለኮቪድ 19 ምን ዓይነት ምላሽ ሰጠ? ለዜጎች የፍትህ ተደራሽነትን እንዲህ ያሉ አዳዲስ ለውጦች ምን ማለት ናቸው?
 • በአገራችሁ የኮቪድ 19 ምላሽ ለመስጠት እስከ አሁን ምን ያህል ብር ወጪ ተደርጓል? በትክክልስ ገንዘቡ ወጪ የተደረገው ለምንድን ነው? ከወጪውስ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የትኛው ነው?
 • ለኮቪድ 19 ምላሽ ለመስጠት ምን ያህል ልገሳ መቀበል ተችሏል? ለጋሾችስ እነማን ናቸው?
 • የማኅበራዊ ወይም አካላዊ ፈቀቅታ የመንግሥት ንግድ ሥራዎች ላይ፣ በማእከል እንዲሁም በክልል መንግሥት ደረጃ፣ ምን ያህል ተጽዕኖ አድርጓል?
 • ወረርሽኙ በአገራችሁ ስላለው የማኅበራዊ ጥበቃ ስርዓት ጥንካሬም ሆነ ድክመት ምን አጋለጠ?
 • በማረሚያ ያሉ ሰዎችን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመጠበቅ ምን ዓይነት እርምጃዎች ተግባራዊ ሆነዋል? በማረሚያ ማዕከላት ወረርሽኝ በሚከሰት ጊዜ፣ ለሕክምና እና መቆጣጠር ምን ዓይነት ስርዓት ተግባር ላይ ውሏል? በዚህ ጊዜ ከማረሚያዎች የሰዎችን ቁጥር የመቀነስ እቅድ አለ?
 • የመከላከያ እርምጃዎች በሚወሰዱ ጊዜ፣ የዜጎች መብቶች እንደተጠበቁ መንግሥት እያረጋገጠ ነው? መንግሥት አስገዳጅ ሕግ ማውጣቱና ተግባራዊ ማድረጉ ምን ዓይነት ስጋት ይኖረዋል? እነዚህስ እንዴት ወደሰብአዊ መብት ጥሰት ሊያደርሱ ይችላሉ?
 • የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት ለተወሰደው የመንግሥት እርምጃ ሕዝብ ምን ዓይነት ግብረ መልስ ሰጠ?
 • የአገራችሁ መንግሥት የኮቪድ 19 ምላሽን የሲቪል መብቶችን ለመጫን፣ መገናኛ ብዙኀንን ዝም ለማሰኘት ወይም ሥልጣንን ለመጠበቅ እንዴት እየተጠቀመበት ይሆን? ለዚህ ምን ማስረጃዎች አሉ? እነማን ናቸው ሥልጣናቸውን ያለአግባብ እየተጠቀሙ ያሉት? በጣም ተጽእኖ የተደረገበትስ ማን ነው?

የጤና ጥበቃ

 • በአፍሪካ በሌሎች ወሳኝ በሆኑ የጤና ፈተናዎች ዙሪያ ይደረጉ የነበሩ የጥናትና ፈጠራ ሥራዎችን የኮቪድ 19 ጥናትና ሕክምና ላይ በምን መንገድ እየተጠቀሟቸው ነው?
 • በአገራችሁ ለኮቪድ 19 ምላሽ በመስጠት ሂደት ውስጥ ፍትሐዊ ያልሆኑ የጤና ተደራሽነቶችን ለመገደብ ምን ዓይነት ዘዴዎች ወደ ተግባር ገብተዋል? በወረርሽኘኙ ምክንያት የጤና አገልግሎት ልዩነት ጨመረ ወይስ ቀነሰ?
 • በምን ዓይነት መንገድ ነው ለኮቪድ 19 ምላሽ ለመስጠት የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለኅብረተሰቡ ለማሳወቅ ጥቅም ላይ የዋሉ ሞዴሎች? የእነዚህ መንገዶች ውስንነት ምኑ ጋር ነው? በተግባር ከዋስ በኋላ እነዚህ ሞዴሎች እንዴት ተቀይረዋል?
 • በእንቅስቃሴ ገደቡ ወቅት የኤች.አይ.ቪ. መከላከል ሥራዎች ቀጥለዋል? አገልግሎት በመስጠት ጊዜ የበገ ፈቃደኞችን፣ የጤና ባለሞያዎችን እና ደንበኞችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ምን ዓይነት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?
 • ከኤች.አይ.ቪ ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች የጸረ ኤድስ መድኃኒት ተደራሽ እንደሆኑ ለማረጋገጥ ምን እየተሠራ ነው? ሕክምና በመስጠትስ ምን ዓይነት ተግዳሮቶች ገጥመዋል? ወርሃዊ ወይም የሚፈለገውን የመድኃኒት መጠን በማቅረብ በኩልስ ምን አዲስ መንገዶች ተፈጥረዋል?
 • የኮቪድ 19 ሕክምናን የሚያገኙ ሕሙማን መብቶች የተጠበቁ ናቸው? የወረርሽኙ ስርጭት ስጋት የሕሙማንን መብት እንዲጣስ ሁኔታዎን እያባባሰ ይሆን? ስለ ሕሙማን መብት የሚታገለው ማን ነው?
 • በአገራችሁ ምን ዓይነት የሕክምና አሠራር ተግባራዊ እየተደረገ ነው? የሕክምና ፕሮቶኮሎቹ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው? የኮቪድ 19 ሕሙማንን በመንከባከብ ሂደት ሐኪሞችና ነርሶች ምን ዓይነት ተግዳሮቶች ገጥመዋቸዋል?
 • ተቋማዊ የሆኑ የለይቶ ማቆያ አካባቢዎች ውስጥ ምን እየተካሄደ ነው?
 • አንድ ሰው ከኮቪድ 19 ካገገመ በኋላ ምን ይደረጋል? በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ ሎች የማስተላለፍ እድላቸው ምን ያህል ጊዜ የሚቆይ ነው? በዚህ ዙሪያ ሳይንሱ ምን ይላል፣ አሁንም ድረስ ያልታወቀውስ ምንድን ነው?
 • የአእምሮ ጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች ምን ዓይነት ድጋፍ አለ? በቤት ውስጥ መቆየት ጊዜ ሊፈጠሩ ለሚችሉ የአእምሮ ጤና ችግሮች የሕክምና ባለሞያዎች ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?
 • ለመድረስ ሩቅ የሆኑና በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ሰዎች ነጻ ወይም በተመጣጣኝ ዋጋ የምርመራና እንክብካቤ ያገኛሉ? ከሕክምና ተደራሽነት መቀነስ የተነሳ ከፍተኛ ስጋት ላይ ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?
 • በአገራችሁ የቤተሰብ እቅድ፣ ቅድመ ወሊድ ምርመራ፣ የወሊድ አገልግሎትና ድኅረ ወሊድ ምርመራ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ያለማቋረጥ እንዲቀጥሉ ለማረጋገጥ የሚያስችል ስርዓት ተግባራዊ ሆኗል? እነዚህስ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን በስርዓት ለማከም ዋስትና ናቸው?
 • የደም ልገሳ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እንዴት ተጽእኖ ተደረገበት? በዚህ ጊዜ የደም አቅርቦት እንዳይቋጥ ለማድረግ የደም ልገሳ ተቋማት ምን እያደረጉ ነው?
 • በኮቪድ 19 ቤት ውስጥ መቀመጥ ግድ ባለበት ሰዓት በሕክምና ሙያ ውስጥ ፋርማሲስት፣ የላብራቶሪ ባለሞያዎች፣ የአየር ቧንቧ ሐኪም ሆነው የሚያገለግሉ ባለሞያዎች ምን ድርሻ እየተወጡ ነው? የእነዚህን ባለሞዎች የሥራ ደኅንነት ለማረጋገጥ ምን ተሠርቷል?
 • በአገራችሁ የጤና እና የወረርሽኝ ቁጥጥር ስርዓት ኮቪድ 19ን መከላከል በሚያስችል አቅም አድጓል? ይህን ለማድረግስ የሚያስፈልገው ሀብት ከየት የሚመነጭ ነው? የሀብት ሽግሽግ ማድረጉ ሌላው ዘርፍ ላይ የሚኖረው ጉዳት ምንድን ነው?
 • በአገራችሁ ወረርሽኙ ያስከተለው የዓለማቀፍ ንግድ መስተጓጎል የመድኃኒት፣ የሕክምና ቁሳቁስ፣ እና ግብዓቶች አቅርቦት ላይ ተጽእኖ አድርጓል? እንዴት? መሠረታዊ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች አቅርቦትን ለማረጋገጥ በመድኃኒት አቅራቢ ቦርድ እና ባለሥልጣናት ምን ዓይነት ስርዓት ተዘርግቷል?
 • የጤና ዘርፉ አቅሙን ሁሉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መቆጣጠር በሆነበት በዚህ ጊዜ፣ በቤተሰብ ውስጥ የታመሙትን በመንከባከብ የተጠመዱ ሴቶች ምን ዓይነት ኃላፊነት ተሸክመዋል? የዚህ የጫና መጨመርስ በሴቶች ምን ያህል ተጽእኖ አሳድሯል? ለእነርሱ የሚሆን ምን ዓይነት ድጋፍ አለ?
 • በመጋቢት መጀመሪያ፣ በርካታ መንግሥታት የመድኃኒት ምርቶችና ግብዓቶች የውጪ ንግድ ላይ ገደብ እንዳኖሩ ይፋ አደረጉ። ይህም ማለት እንደ ፓራስታሞል ካሉ መድኃኒቶች ጀምሮ፣ ለአፍሪካ ይህንን ከሚያቀርቡ የመድኃኒት አቅራቢዎች የነበረው የአቅርቦት አገልግሎት ተረበሸ ማለት ነው። አገራችሁ ታድያ በዚህ ምክንያት ተጎድታለች? በቀነሰው የውጭ ገቢ ንግድ ምክንያት የተፈጠረውን ቀዳዳ ለመድፈን ምን ዓይነት የድንገተኛ አደጋ እቅዶች ተይዘዋል?
 • ለሕዝብ ይሰራጭ የነበረውን ንጽህና እና የተመጣጠነ ምግብ የተመለከተ መልዕክት የኮቪ 19 ወረርሽኝ በምን መንገድ ቀይሮታል ወይም ቀርጾታል? ለዚህ አዲስ መልዕክትስ የዜጎች ግብረ መልስ በአገር ዐቀፍ ደረጃ ምን ይመስላል?
 • ተማሪ ዶክተሮችና ነርሶች ለሆፒታሎች ይሰጡ የነበረውን አገልግሎትና ድጋፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መዘጋት ተጽእኖ አሳድሮበታል? ብዙ ተማሪዎች በጣም አስፈላጊ የሆኑ እንደ ሕሙማንን መከታተል፣ አልጋ እና መድኃኒቶች መመደብ ላይ እያገዙ ነው። ይህ ታድያ በሆስፒታል ሠራተኞች ላይ ጫናው እንዲጨምር አድርጓል? ከተዘጉ ተቋማት ያሉ መምህራንስ ለድጋፍ የሆስፒታል ሠራተኞችን እየተቀላቀሉ ነው? እንዴት?
 • በአገር ደረጃ በሆስፒታሎች በሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ቫይረሱ እንዳይስፋፋ ምን ዓይነት እርምጃዎች ተተግብረዋል? የጤና ባለሞያዎችስ ለኮቪድ 19 ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?
 • የኮቪድ 19 የስልክ ጥሪ ማእከሎች እንዴት ቀጠሉ?
 • ተቋማዊ ለይቶ ማቆያ ስርዓት እንዴት ነው እየሠራ ያለው? ቫይረሱ ይኖርባቸዋል ተብሎ የተጠረጠሩ ወይም ከፍተኛ ስጋት ካለባቸው አገራት የመጡ ሰዎች ለይተው እንዲቆዩ በሚደረጉባቸው በእነዚህ ቦታዎች ምን ይካሄዳል?
 • አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት፣ አየር መንገድና በድንበር መግቢያዎች አካባቢ ጉቦዎች ይሰጣሉ፣ ይህም ሰዎች ራሳቸው ወይም የቅርብ ዘመዳቸው ለይቶ ማቆያ እንዳይገቡ የሚፈልጉ ሰዎች የሚያደርጉት ነው። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? የትኞቹ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወይም ግለሰበቦች በዚህ ውስጥ እጃቸው አለበት?
 • በአልጋ፣ ባለሞያና ቁሳቁስ አንጻር ብሔራዊና ክልላዊ የሪፈራል ሆስፒታሎች አቅም ምን ያህል ነው?
 • የክልል ሪፈራል ሆስፒታሎች ምንአልባት እጅግ ሰፊ ለሆነ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እንዴት እየተዘጋጁ ነው? የሕክምና አገልግሎቶችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ለድንገተኛ የሚሆኑ ምን ዓይነት እቅዶች በተግባር ላይ ይገኛሉ?
 • ሆፒታሎች በኮቪድ 19 ሕሙማን ቢጥለቀለቁ፣ ለድንገተኛ የሚሆኑ ምን ዓይነት እቅዶች ተግባራዊ ሆነዋል? የጤና ሠራተኞችና ባለሞያዎችስ እነዚህን እቅዶች እንዴት ይተገብራሉ?
 • ሀብትን ኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየዋለ ባለበት ሁኔታ፣ አገራት ለአሁንና ለወደፊት የወረርሽኙ ስርጭት ስጋት የአገራት ዝግጁነት እንዴት ነው? ኮቪድ 19 የነበረውን የበሽታ ጫና የባሰ አክፍቶታል?
 • ኮቪድ 19 በአገራችሁ ስላለው የጤና አገልግሎት ጥንካሬ ወይም ድክመት ምን አጋለጠ?
 • ለቫይረሱ መድኃኒት ወይም ክትባት ለማግኘት በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ምን ዓይነት ጥረቶች እየተደረጉ ነው?
 • የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንዴት ነው የሚሠራው?

ሠራተኛ/የሰው ኃይል

 • ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት ጀምሮ የየትኞቹ የሠራተኞች አገልግሎት ፍላጎት ቀነሰ?
 • በቤት ውስጥ መቆየት ግድ በተባለበት ጊዜ ጊዜያዊ እና ተንቀሳቃሽ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ዕጣ ምንድን ነው? ለእነዚህ ሰዎች የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥበቃ አለመኖር መንግሥት እንዴት ያለ ምላሽ እየሰጠ ነው?
 • በአገራችሁ የቀጣሪዎች አጠቃላይ የጤና እና ደኅንነት ግዴታዎች ምን ምን ናቸው? ቀጣሪዎችስ የሠራተኞችን ደኅንነት ከመጠበቅ አንጻር ያሉ የመንግሥትን መመሪያዎችን እየተገበሩ እንደሆነ ለማረጋገጥ ምን እየተደረገ ነው?
 • በበርካታ አገራት የውጭ አገር ቅጥር አገልግሎት ከመቅረቱ አንጻር፣ በውጪ ሠራተኛና አሠሪ አገናኝ ኩባንያዎች ለተቀጠሩ ሰዎች ምን ድጋፍ አለ? ምንአልባት ካለ፣ ከአገራችሁ የዲፕሎማሲ ተቋማትስ ምን ድጋፍ እያገኙ ነው?
 • በቦታ ቦታ በሚደረግ እንቅስቃሴ እና የሥራ መረበሽ ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ የተጎዱ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው? ትምህርት፣ ቱሪዝም፣ መዝናኛ፣ መስተንግዶ፣ ኤሌክትሮኒክስ ወይስ የቅንጦት ዕቃዎች ሽያጭ? በእነዚህ ዘርፎች የተቀጠሩ ሠራተኞች ላይስ ይህ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል? ይህስ ለኢንቨስትመንትና የማስፋፋት እቅድ ምን ተጽእኖ አለው?

የኑሮ ሁኔታ

 • ወረርሽኙ ወደ አገራችሁ የሚመጣ ሰብአዊ ድጋፍ ላይ ተጽእኖ አድርጓል? ለድጋፍ ይውላሉ ተብለው የተያዙ ሀብቶች ኮቪድ 19ን ለመከላል ለሚደረግ ጥረት እየዋሉ ነው? ምን ውጤትስ አመጡ?
 • በአገራችሁ ስላለው የማኅበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ እኩልነት አለመኖር ኮቪድ 19 ምን አጋለጠ? በግልጽ የታዩ እውነቶችን በሚመለከት መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዴት ምላሽ እየሰጡ ነው?
 • ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሰዎች ይደረግ የነበረው ድጋፋና እርዳታ በወረርሽኙ ምክንያት ተቋርጧል? ይህ ተጋላጭ ለሆኑ በተለይም ሴቶችና ሕጻናት ምን ዓይነት አደጋ የሚደቅን ነው?
 • የውሃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች የኮሮና ቫይረስ መከላከል ሥራው እንዴት እየተተገበረ ነው? በዚህ ጊዜ ንጹህ ውሃ ለማቅረብ እየሠሩ ያሉ መንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አሉ?
 • የኮቪድ 19 የስርዓተ ጾታ መለኪያዎች ምንድን ናቸው? ባለው የእንቅስቃሴ ገደብ፣ የትምህርት ቤት መዘጋትና የምጣኔ ሀብት መቀዛቀዝ ሴቶች እንዴት ተጎዱ?
 • በቤት ውስጥ መቀመጥ ግድ በተባለበት ጊዜ የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች ትኩረት ተሰጥቷል? ለእነርሱ ተገቢና ምቹ በሆነ መንገድ በመገናኛ ብዙኀን፣ በማኅበረሰብ ወይም የመንግሥት የዜና ማሰራጫዎች መረጃ ማግኘትስ ችለዋል? አካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች ከመንግሥት፣ በሲቪል ማኅበራትና ማኅበራዊ ተቋማት ምን ዓይነት የድጋፍ አካሄዶች ተግባር ላይ ናቸው?
 • አስፈላጊ የሚባሉ እንደ ሕክምና እና የውሃ አቅርቦት ዓይነት አገልግሎቶች ማነስ ምክንያት የስደተኞች መጠለያዎች በኮቪድ ክፉኛ ሊመቱ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ። ስደተኞች የሚገኙባቸው አገራት ለዚህ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?
 • ከፍተኛ ጥግግት ባለባቸው የስደተኛ መጠለያዎችና ካምፖች ውስጥ ከቤት ያለመውጣት መመሪያዎች በምን መንገድ እየተተገበሩ ነው?
 • የድንበር መዘጋት ድንበር አካባቢ የሚገኙ ሕዝቦችን የምጣኔ ሀብትና የማኅበራዊ ሕይወት ላይ እንዴት ተጽእኖ አደረገ?
 • የአገራችሁ መንግሥት መደበኛ ባልሆነ አሰፋፈር የሚኖሩ ሰዎችን ፍላጎት እንዴት እያሟላ ነው? በእነዚህ ማኅበረሰቦች ውስጥ ቫይረሱን ለመከላከል፣ ለመመርመርና ማከም አገልግሎትን እየሰጠ ነው?

ሰዎች/ግለሰቦች

 • በአገራችሁ ኮሮና ቫይረስን በዝምታ እየተዋጉ ያሉ ጀግኖች እነማን ናቸው? ኮቪድ 19ን በሚመለከት ለሕዝብ መረጃዎችን ለማድረስ፣ ለጤና ተቋማት ምላሽ ለመስጠትና የማኅበራት ጥረቶች ላይ ፊት ለፊት ግንባር ሆኖ የሚገኘው ማን ነው? የቻላችሁትን ያህል ፕሮፋይል አድርጉ፤
 • የኮቪድ 19 ሕሙማንን በማከም ግንባር ላይ የሚገኝ የሕክምና ባለሞያ መሆን ምን ዓይነት ስሜት አለው?
 • በወረርሽኙ ወቅት የበለጠ ተጋላጭ የሆነ ማኅበረሰብን ለማገዝ ምን ዓይነት ማኅበራዊ የፈጠራ ሥራዎች ተሠርተዋል ወይም እየተሠሩ ነው?
 • ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሕክምናውንና ሆስፒታል መቆየቱን እንዴት እየተወጡት ነው?
 • ኮቪድ 19 በሕሙማን፣ በሕሙማን የቅርብ ዘመዶችና ተንከባካቢዎች ዕይታ ምንድን ነው?
 • ቫይረሱ አለባቸው ተብለው ተጠርጥረው ነገር ግን ነጻ በሆኑ ሰዎች ዕይታ ኮቪድ 19 ምንድን ነው?
 • ከበሽታው ባገገሙ ሰዎች ዕይታ ኮቪድ 19 ምንድን ነው?
 • በአገራችሁ ያሉ መሪዎች ኮቪድ 19ን ለመከላከል ምን ዓይነት የግል ጥንቃቄ እያደረጉ ነው?

የሕዝብ ሥራዎች እና መሠረተ ልማት

 • በምጣኔ ሀብት መቀዛቀዝና መዘጋጋት ምክንያት የትኛዎቹ መሠረታዊ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተጎድተዋል? የትኞቹ ቁልፍ የመጠናቀቂያ ጊዜዎች ሊያልፉ ወይም ሊያመልጡ ይችላሉ? እነዚህ ፕሮጀክቶች በጊዜው ለማጠናቀቅ እንዲቻል የገንዘብና የሰው ኃይል መለያየት ሳይፈጠር ለመቆየት ምን ዓይነት ስልቶች ተግባር ላይ ውለዋል?
 • በቻይና የገንዘብ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ወይም በቻይና ኩባንያዎች እየተተገበሩ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በኮቪድ 19 እንዴት ይጎዳሉ?

ሐይማኖት

 • በአገራችሁ አማኝ ማኅበረሰቦች ለወረርሽኙ እንዴት ምላሽ እየሰጡ ነው?
 • የእንቅስቀሴ ገደቡ በአገራችሁ ያሉ ሃይማኖታዊ አገልግሎቶችን እና የእርዳታ ማሰባሰቦችን እንዴት ቀየረው?
 • ሃይማኖታዊና የተቀደሱ ስፍራዎች እንዲሁም ሌሎች በአፍሪካ የአምልኮ መፈጸሚያ ቦታዎች መሄድ ተከልክሏል? አጥባቂ የእምነት ሰዎች እነዚህን እርምጃዎች እንዴት ተለማመዷቸው/ተቀበሏቸው?
 • በአገራችሁ ኮቪድ 19 በሳይንስና በሃይማኖት መካከል ያለውን ልዩነት አጠበበው ወይስ አሰፋው? በእነዚህ የሐሳብ ልዩነቶች ዙሪያ ምን ዓይነት ሙግቶች እየተካሄዱ ነው?
 • በአገራችሁ የሃይማኖት መሪዎች ሃይማኖታዊ ምስጢራትን ለመፈጸምና ለማኅበረሰቡ እንዲሁም ለሰዎች የሚፈልጉትን መንፈሳዊ ስርዓት ለመከወን እንዴት ተደግፈዋል? የእንቅስቃሴ ገደብ እርምጃው እነዚህን አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ ፈቅዶላቸዋል? ካልሆነ፣ የሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት ምን እያደረጉ ነው?
 • የሃይማኖት መሪዎች በዚህ ወቅት ለምዕመናኑ ምን ዓይነት አባታዊ ድጋፍ ወይም ጥበቃ ለመስጠት ችለዋል? እንዴትስ ነው ያንን እያደረጉ ያሉት?
 • የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመቆጣጠር በአዎንታም ሆነ በአሉታዊ መንገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ያሉ የሃይማኖት መሪዎች አሉ? ምን ያህልስ ተጽእኖ መፍጠር ችለዋል?
 • በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የሃይማኖት ተቋማት ምን ዓይነት ድርሻ እየተወጡ ነው?
 • በዚህ ወቅት በአገራችሁና በአካባቢያችሁም ያለው የአምልኮ ሁኔታ ምን ይመስላል?

ስፖርት፣ ጥበብ እና መዝናኛ

 • በአገራችሁ የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ መደረጉን ተከትሎ፣ ተጫዋቾችን ለመደገፍ የሚያስችል ማንኛውም ዓይነት የድጋፍ ፕሮግራሞች አሉ?
 • ኮቪድ 19 የሰዎችን አካላዊ እንቅስቃሴ እና ልምድ እንዴት ቀየረው?
 • የሙዚቃ ድግሶች፣ የኪነጥበብ ክዋኔዎች እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በመሰረዛቸው ምክንያት ምን ያህል ገቢ ሳይገኝ ቀረ? ወደፊት ይህን ገቢ መልሶ ለማግኘት ምን ዓይነት ስልቶች እየተዘጋጁ ነው?
 • የስፖርት ሰዎች በዚህ እንቅስቃሴ በተገደበበት ጊዜ ምን እየሠሩ ነው? ቡድኖች እና የቡድን አመራሮችስ የተጫዋቾችን ጉዳት ለመቀነስ በተለይም ንክኪን ግድ በሚሉ ስፖርት ውስጥ ያሉትን፣ ምን እየሠሩ ነው?
 • ክውን ጥበባት ላይ የሚሠሩ ሰዎች የእንቅስቃሴ ገደቡን እንዴት እየተወጡት ነው? የበለጠ የተጎዳው ማን ነው?
 • የስፖርት እና መዝናኛ ዘርፍ ላይ ያሉ ዝነኞች ያላቸውን አውድ ሰዎችን ስለ ኮቪድ 19 መከላከል ዘዴዎች ለማሳወቅና ለማስተማር እንዴት እየተጠቀሙበት ነው? እየመሩ ያሉ እነማን ናቸው፣ ምን ያህልስ ተጽእኖ መፍጠር ችለዋል?
 • በዚህ ጊዜ በኢንተርኔት የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ከተመልካቾቻቸው ጋር እየተገናኙ ያሉ የትኞቹ አርቲስቶች ናቸው? ከእነርሱም አንዳቸውስ እነዚህን ቻናሎች ወደ ገንዘብ ቀይረዋል?

ማጠቃለያ

 • የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ አንዴት ምላሽ ሰጡ?

ይህ ዘገባ አስቀድሞ በአፍሪካ የሚድያ ልህቀት ማእከል ድረገጽ ላይ የወጣ ሲሆን፣ በዚህ ለንባብ የቀረበው ፈቃድ በመገኘቱ ነው። ተጨማሪ ሐሳቦችንና ቢሆኑ የምትሏቸውን በማእከሉ ድረገጽማኅበራዊ ገጾች አልያም በኢሜይል መላክ ትችላላችሁ።

የአፍሪካ የሚድያ ልህቀት ማእከል መቀመጫውን በካምፓላ ያደረገ፣ ራሱን የቻለ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ የሙያ ድርጅት ነው። በትኩረት የሚሠራውም በአፍሪካ በጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ልህቀት ለመፍጠር ነው። ይህ ማእከል የረጅም ጊዜ አካሄዶችን ተጠቅሞ የሚሠራ ሲሆን፣ በዚህም ተግባራዊ ሥልጠና እና ወርክሾ በተለያዩ ልምምዶችና ግንዛቤ ስጨበጫዎች ይካሄዳል።

Republish our articles for free, online or in print, under a Creative Commons license.

Republish this article


Material from GIJN’s website is generally available for republication under a Creative Commons Attribution-NonCommercial 4.0 International license. Images usually are published under a different license, so we advise you to use alternatives or contact us regarding permission. Here are our full terms for republication. You must credit the author, link to the original story, and name GIJN as the first publisher. For any queries or to send us a courtesy republication note, write to hello@gijn.org.

Read Next

የሪፖርት ማድረጊያ መሳሪያዎች እና ጠቃሚ ምክሮች

ጠቃሚ ምክሮች ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች

አዲስ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የዓለማችን ትልቁ ዜና ሆኖ ቀጥሏል። እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እስከ አሁን የኮሮና ቫይረስ ከ167 በላይ የዓለም አገራትን አዳርሶ፣ 11 ሺሕ በላይ ሰዎችን ገድሏል። ከ286 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል።

የናይጄሪያው ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) በኮቪድ 19 ምላሽ ተጠሪነትን ለመፍጠር እያደረገ ያለው ግፊት

መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።