የኦንላይን የምርምር መሣሪያዎች/
Read this article in
በቢቢሲ ቁጥር አንድ በሚለው የኦንላይን መርማሪው ፖል ማየርስ የቀረበው ኦንላይን የጥናት መሣሪያዎችና የምርመራ ዘዴዎች ለዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ አንባቢዎች የኦንላይን የጥናት ፍለጋዎች መነሻ ሆኖ አገልግሏል። ይህ የእርሱ ‹ሪሰርች ክሊኒክ› የተባለ ድረገጽ፣ የብዙ ጥናታዊ ሥራዎች ሊንክ እና የ‹ጥናት ግብዓቶች› ይገኙበታል።
ማየርስ በ2019 የኔትወርኩ ዌብናር ላይ ሰዎችን ኦንላይን እንዴት እናገኛለን ለሚለው ጠቃሚ ምክሮችን አቅርቧል። የዓለማቀፉ ኔትወርክ ማየርስን ያቀረበውን በጽሑፍ አሰናድቶ ነበር። አራት ጥያቄዎች፣ በኦንላይን ምርጡ መርማሪ ፓውል ማየርስ።
እዚህ ላይ ‹gijn.org› ላይ የሚገኙ የማየርስን ሌሎች መመሪያዎች ተመልከቱ፤
ትዊተርን በመጠቀም ሰበር ዜና በሚገኙባው ቦታዎች የነበሩ ሰዎችን ለማግኘት
ለድረገጽ መፈለጊያ ብራውዘርን በቅርብ ማስቀመጥ፣
የዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ የምርመራ መሣሪያዎች መገኛ (Toolbox)፣ በኔትወርኩ አባል አላስታየር ኦቴር የተዘጋጀ አንድ ጽሑፍ፣ የተመረጡ ርእሰ ጉዳዮችን ይቃኛል፤
- ስሞችን እና ድረገጾችን መፈለግ፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ማረጋገጥ፣ የመፈለጊያዎች ክምችት
- ሰዎች መፈለግ፣ ድሮችን መበርበርና ራስን ደኅና ጠብቆ ማቆየት
- ለሰዎችና ኩባንያዎች የኋላ መነሻ መስጠት
- ትዊተርን መበርበርና የድረገጾች አዲስ መረጃ መከታተል
- ከመረጃ ትንታኔ ባሻገር ድረገጽ ላይ በጥልቀት መፈለግ
ጄክ ክሪፕስ በብሎጉ ላይ በቋሚነት ጠቃሚ ነጥቦችን ያጋራል። osintpodcast.com ላይ በሚገኝ ፖድካስት ላይ አስተዋዋቂ ነው። በሕዝብና የግል ዘርፉ ላይ ልምድ ያለው የወል/የሕዝብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ኢንተለጀንስ ተንታኝ ነው።
OSINTcurio.us ሳምንታዊ ፖድካስቶችን፣ ዌብካስቶችና ለዐስር ደቂቃ የሚያቀርቡ ጠቃሚ ነጥቦችን በተንቀሳቃሽ ምስል ያቀርባል። በዚህም የተለያዩ የወል ምንጭ የምርመራ መንገዶችን ይሸፍናል። ይህም የማኅበረሰብ ፕሮጀክት ሲሆን፣ በ2018 መጨረሻ አካባቢ በዐስር አቅራቢ ባለሞያዎች የተጀመረ ነው።
Sector035, <Just a shadowy nerd> በሚል ቅጥያ የሚጠራ ሲሆን፣ በየሳምንቱ ጠቃሚ ነጥቦችን ያቀርባል። በተለይም የመልክዓ ምድራዊ መገኛን በሚመለከት። Week in OSINT እና Quiztimeን ያሳትማል።
የአንድን ሰው ማን፣ ከየት እና መቼ የሚሉ ጉዳዮች የሚመረምር የኦንላይን ዘዴ። ይህም ሌላው በኢንተርኔት መፈለጊያ ዝርዝር ባለሞያ በሆነው ሔንክ ቫን ኤስ የተዘጋጀ ነው። ማን ምን ፖስት አደረገ፣ (Who Posted What) የሚለውንም ተመልከቱ። ይህም የቫን ኢስ ሐሳብ ሆኖ፣ በዳንኤል ኤንድሬስ የዳበረ ሲሆን፣ በፌስቡክ ገጽ ላይ ቁልፍ የሆነውን አንድ ቃል በማስገባት፣ በተወሰነ ጊዜ ወይም በተሰጡ ጊዜያት መካከል ፖስት የተደረጉ ተመሳሳይ ቁልፍ ቃላትን የሚፈልግ ነው።
የወል/ሕዝብ መረጃ ምንጮች ኢንተለጀንስ ማዕቀፍ የተብራራ እና በየጊዜው የሚጨምሩ ለምርመራ ሥራ የሚያገለግሉ የዲጂታል መሣሪያዎች ዝርዝር የያዘ ነው።
ውስብስብ የሆነ ድርን በጥልቀት መመርመር፣ በጄኒና ሴግኒኒ፤ ውስብስብ ለሆኑ የጎግል ማሰሻዎች የሚረዱና የተሻሻሉ ጠቃሚ ነጥቦች በመጥቀስ ይጀምራል። በዚህ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የመረጃ ጋዜጠኝነት ፕሮግራም የጋዜጠኝነት ትምህርት ዳይሬክተር የቀረበ ገለጻ፣ ጉግል እንደ ድልድይ በመጠቀም ለምሳሌ የአደገኛ እጽ ዝውውርን በሚመለከት ድሮችን በጥልቀት ወደ መመርመር ተሻግሯል።
እንዴት የድር ጥልቅ መርማሪ መሆን እንደሚቻል. ይህ የግሎባል የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ ጽሑፍ፣ በጀርመናዊው ጋዜጠኛ፣ ተመራማሪና በ11ኛው የግሎባል የምርመራ ጋዜጠኝነት ኮንፈረንስ አሠልጣኝ፣ በአልብሬት ኡዴ የተሰጠውን ምክር ያብራራል። ኡዴ እንደሚለው፣ የማሰሻ ማንቀሳቀሻዎች በድር ላይ ጥልቅ ምርመራ ለማድረግ ምንም የሚሰጡት ዋጋ የለም። እናም የእርሱ ምክር በተለየ መንገድ ማሰብ የሚል ሲሆን፣ ተጨማሪ ነጥቦችንም አክሏል። ተያያዥ ብሎ ያሰፈራቸውን ጠቃሚ ነጥቦች በዚህ ተመልከቱ፤ ዳታቤዝን መፈለግና መጠቀም (Finding and using databases)
የተሻሉ/የረቀቁ የጎግል ማሰሻዎች/መፈለጊያዎች
የጎግልን የረቀቁ የመፈለጊያ ገጽ እና የመፈለጊያውን መመሪያዎችን መጠቀም። በተያያዘ ጎግል የመፈለጊያ ትምህርቶችን ጨምሮ ‹ፓወር ሰርቺንግ› ኮርሶችን እና ሌሎችንም በሚመለከት ለጋዜጠኞች ሥልጠና ይሰጣል።
ቁልፍ ለሆኑ የመመሪያዎች ዝርዝር፣ በፖል ማየርስ የተዘጋጀውን ‹Google’s Advanced Search Syntax› ይመልከቱ፤
መሠረታዊ ጉዳዮችን ለማወቅ በ‹ኤክስፐርቲዝፋይንደር› የተዘጋጀውን ‹Google Search Tips for Journalists› ይመልከቱ፤
ከዛም ተከታዮቹን ሞክሩ፣
የዳንኤል ረስል የመፈለጊያ ጥናት እና የእርሱ የጉግል የረቀቁ የመፈለጊያ ኦፕሬተሮች
ኮፎርጅ ከተባለው የአይቲ ኩባንያ ኤሪክ ሜሊሉ ያዘጋጀው፣ ምርጥ ለሚባል ኀሰሳ የሚረዱ 37 የረቀቁ የጎግል መፈለጊያ ጠቃሚ ነጥቦች
ከኦቤርሎ ኩባንያ በዴቪድ ቭራኒካር የተዘጋጀ፣ የጎግል የረቀቁ መፈለጊያዎች፣ ለተሻሉ ፍለጋዎች ጠቃሚ ነጥቦችና አሠራሮች
ኪ-ወርድ ቱል ከተባለ ብሎግ የተገኘ፣ ጎግል የረቀቀ መፈለጊያ፣ የተሻለ መረጃ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል (2 እጥፍ የሚፈጥን)
የጉግል መፈለጊያ ኦፕሬተሮች፤ ሙሉ ዝርዝሮች (42 የረቀቁ ኦፕሬተሮች) በጆሹዋ ሀርድዊክ
ከሳን አንቶኒዮ ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ቤተመጻሕፍት የተገኘ፣ የረቀቀ የጎግል መፈለጊያ
የኤዮጋን ስዌኒ የፈጠራ ውጤት የሆነው ‹OSINT Essentials›፣ ለኦንላይን ማጣራት ሥራዎች፣ ለዲጂታል ጋዜጠኝነት እና ለወል የመረጃ ምንጭ ኢንተለጀንስ ሥራ የሚጠቅሙ፣ ነጻ መሣሪያዎችና አገልግሎቶችን ማግኛ ሊንኮችን የሚያቀርብ ነው።
‹First Draft› ዓለማቀፍ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ የተሻሉ ጠቃሚ መሣሪያዎችን ሰብስቦ በመያዝ ጋዜጠኞችን የሚደግፍ ነው። በተያያዘ ‹First Draft’s Essential Guide to Verifying Online Information› (2019) በሚል ርዕስ የሚገኝ የፒዲኤፍ ሰነድና ተያያዥ የሥልጠና ግብዓቶችን ማየት ይቻላል፤
በደቡብ አፍሪካ ጋዜጠኛና አሠልጣኝ ሬይሞንድ ጆሴፍ የተዘጋጀ፤ መሣሪያዎች፣ ጠቃሚ ሊንኮችና ግብዓቶች፤ በትዊተር፣ ማኅበራዊ ሚድያ፣ ማጣሪያ፣ ዶሜይን እና የአይፒ መረጃ፣ ዓለማቀፍ የስልክ ደብተሮች እና ሌሎችም ላይ የሚገኝ የመረጃ ገጽ ነው። ጆሴፍ በሰጠው ገለጻም፣ እንዴት የዲጂታል መርማሪ መሆን ይቻላል የሚለውን አብራርቷል።
የማይታየውን ማጋለጥ፣ (Exposing the Invisible) በገጹ የተለያዩ መመሪያዎች ያሉት ሲሆን፣ ‹ጎግል ዶርኪንግ›ን ያካትታል። ብዙኀን በሚጠቀሙባቸው ድረገጾች የተደበቁ መረጃዎችን እና የኅብረሰተብ በሆኑ ሰርቨሮች ያሉ የተጋለጡ ክፍተቶችን በሚመለከት መፈለጊያዎችን መረጃ መጠየቂያ ዘዴ ነው።
በፋይናንሻል ታይምስ ከፍተኛ የዜና ክፍል ባለሞያ የሆነው ማክስ ሐርሎስ ያዘጋጀው፣ መመሪያው ምን ያህል እንደሚያስኬድህ በሚገባ ማወቅ የሚለውን በሚመለከት ገለጻ አድርጓል። የሚቻለው የትኛው ነው? እርሱም ሲያጠቃልል እንዲህ አስቀመጠው፣ የድረገጹን ባለቤት እወቅ፣ በብርሃን ፍጥነት መረጃዎችን ተንትን፣ በተለያየ መንገድ የተጻፉ ሥሞችን አዛምድ፣ መረጃዎችን ከኦንላይን ዳታቤዝ ጋር አገናኝ/ሊንክ አድርግ፣ ከመቶ በላይ ሰነዶችን በብዛት መፈለግ።
‹AML RightSource› በአሜሪካ የግል ተቋም ነው። በዋናነት ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው በጸረ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ የባንክ ምሥጢራዊ እንቅስቃሴ እና የገንዘብ ነክ ወንጀሎችና መፍትሄአቸው ላይ ነው። የምንጮችን ስብስብም በአንድ ላይ ያስቀምጣል።
የምርመራ ጋዜጠኛና ኤዲተር በሆነው በዳውግ ሐዲክስ የተዘጋጀው ‹Investigate with Document Cloud› ይህም 1.6 ሚሊዮን የሚሆኑ፣ ጋዜጠኞች ያጋሯቸው፣ የሕዝብ ሰነዶችን መጠቀሚያ መመሪያ ነው። ይህም የራስን ሰነድ መተንተን፣ ከሌሎች ጋር መተባበር፣ የዶክመንት ሥራውን ሂደት መምት እና ኦንላይን ሥራዎችን ማጋራትን ያካትታል።
Malachy Browne’s Toolkit. ከ80 በላይ የወል የሆኑ ምርጥ በሚባ መርማሪዎች የቀረቡ የምርመራ መሣሪያ ሊንኮች ያሉት ነው። ይህን በሚመለከት የኒውዮርክ ታይምሱ ከፍተኛ አዘጋጅ በገለጻው ሲያስረዳ፣ ሁሉም የገለጻው ታዳሚዎች ማለት ይቻላል፣ እንዲጠቀሙበት ለማግኘት ጠይቀዋል።
‹An Investigative Guide to LinkedIn› በ2019 ለቤሊንግካት በናታን ፓቲን የተሠራ ነው። ይህ መመሪያ የሊንክዲን ፕሮፋይሎችን ለመለየት እንዲቻል ጠቃሚ መሣሪያዎችን እና ዘዴዎችን ለማቅረብ ያለመ ነው። ይህም የተፈለገውን ሰው ፕሮፋይል በሌሎች ማኅበራዊ ሚድያዎች ውስጥ ለመቃኘት ያስችላል።
‹A Guide to Open Source Intelligence (OSINT)› በሚካኤል ኤዲሰን ሀይደን የተዘጋጀ፣ በኮሎምቢያ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቶው ለተባለ የዲጂታል ጋዜጠኝነት ማእከል በ2019 የተዘጋጀ ሲሆን፣ ተከታዮቹን ጉዳዮች ሽፋን ሰጥቷቸዋል፤
- በክፍት እና ዝግ ኔትወርኮች መካከል ያለው ልዩነት
- የወል በሆኑ ድሮች ላይ መፈለግ
- የማኅበራዊ ሚድያ አካውንቶች እውነተኛ መሆናቸውን ማጣራት
- ምስልና ቪድዮዎችን ማጣራት/ማረጋገጥ
- የተዘነጉ ድረገጾችን ማሰስ
- አርካይቮችን መጠቀምና ሥራዎችን ማስቀመጥ
- አዳዲስ አውዶችን ማወቅና ከአዳዲስ ኅብረቶች ጋር ግንኙነት መፍጠር
Finding Former Employees, በጄምስ ሚንዝ የቀረበ ሲሆን፣ እንደ ሚንዝ ግሩፕ መሥራችና ፕሬዝዳንቱ ጄምስ ከሆነ፣ ‹በምርመራ አዘጋገብ ከፍተኛ አቅም የሚሰጡ ዐስር ነጥቦች፤ የቀደሙትን ማግኘት› ወሳኝ ነው።
‹Tools and tips for digging into Facebook from two investigative journalists› (ከኹለት የምርመራ ጋዜጠኞች የተገኙ ፌስቡክ ውስጥ ፍለጋን ለማድረግ የሚረዱ ጠቃሚ መሣሪያዎችና ነጥቦች) ይህ በ2019 ከብሩክ ዊልያምስ እና ሔንክ ቫን ኤስ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ ነው። ዊልያም ተሸላሚ የምርመራ ዘጋቢ ሲሆን፣ በቦስትን ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ ጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ነው። ሔንክ ቫን ደግሞ ለ‹ Bellingcat.com› መሪ መርማሪ ነው።
Investigative Research Links (የምርመራ ጥናት ማግኛ/ሊንኮች)ከጥናት ኤዲተሯ ማርጎት ዊልያም፣ የምክረ ሐሳቦችን ስብስብ ከ‹ Effective Google Searching› እስከ የ‹Research Guru› ዝርዝሮች ድረስ ገጾች በመውሰድ ያቀርባል። በተያያዘም ለምርመራ ፕሮጀክቶች የጥናት እቅድ የሚለውን ጠቃሚ ነጥቦች የሚገኙበትን ዝርዝር መመልከት ይቻላል።
Bellingcat’s Online Investigative Toolkit (የቤሊንግ ካት ኦንላይን መመርመሪያ መሣሪያዎች መገኛ) ይህም በካርታ፣ መልክዓ ምድራዊ ፍለጋ፣ ምስል፣ ማኅበራዊ ሚድያ፣ ትራንስፖርት ባለሞያና መሰል ሰፊና የተለያ ምንጮችን ያካተተ ነው፤
‹Bureau Local collaborative tools› ከ80 በላይ ዝርዝር ምንጮችን የያዘ፣ ከእነዛም ውስጥ አንዳንዶቹ ለምርምር የሚያግዙ መሣሪያዎች ናቸው። ይህም መቀመጫውን በኢንግሊዝ ያደረገው የምርመራ ጋዜጠኝነት ቢሮ ቀረበ ነው።
‹Tools for Reporters› በሴማንታ ሱሜ፣ በአዳዲስ ዘዴዎች መደበኛ ኢሜይል አድራሻዎችን ይይዛል፣ ለምሳሌ መገኘት የማይፈልጉ ኢሜይሎችን ማግኘት።
‹Fundamental search for journalists› (የጋዜጠኞች መሠረታዊ መፈለጊያዎች) ይህ በቪንሰንት ራየን አስተማሪነት ተከታታይ የኦንላይን ትምህርቶች ከ‹Datajournalism.com› የሚሰጥበት ነው። የረቀቁ መፈለጊያዎች፣ ማጣሪያዎች፣ ማሳያዎችና መልክዓ ምድር ጠቋሚዎችን ያዳርሳል፤
‹SPJ Journalist’s Toolbox› በአሜሪካ ካሉ የጋዜጠኝነት ባለሞያዎች ኅብረት የተገኘ፣ በማይክ ሬይሊ የተፈጠረ ነው። የተለያዩና በርካታ መሣሪያዎችን ያካተተ ነው፤
‹IntelTechniques› በሚካኤል ባዘል የተዘጋጀ ገጽ ነው፣ እርሴም የቀድሞ የአሜሪካ መንግሥት የኮምፕዩተር ላይ ወንጀሎች መርማሪ ሲሆን፣ አሁን ደራሲና አሠልጣን ነው። የራሱን ‹The Privacy, Security, & OSINT› የሚለውን መሰናዶ በራሱ የራድዮ ስርጭቶች ይሠራል፣
‹How to find an academic research paper› (ትምህርታዊ የጥናት ወረቀቶችን እንዴት መፈለግ እንደሚቻል) በዴቪድ ትሪሊንግ፣ ለ‹ጆርናሊስትስ ሪሶርስ› ጸሐፊ ነው። ይህም መቀመጫውን በሀርቫርድ በሾረንስታይን የሚድያ፣ ፖለቲካና የኅብረተሰብ ፖሊሲ ማእከል ያደረገ ነው፤
‹World.192.com፣ ዓለማቀፍ የስልክ መምሪየዎች ዝርዝር ያለው፤
‹Using Phone Contact Book Apps For Digital Research› (ለዲጂታል ፍለጋ የስልክ ቁጥሮች ማቆያ መተግበሪያን መጠቀም) በቤሊንግካት በሚሠራው ኤሪክ ቶለር የተዘጋጀ የ2019 ፖስት የተደረገ መመሪያ፣
‹Use Chrome Developer Tools to View Masked Phone Numbers for Free on a Popular People Search Site› (የተደበቁ ስልክ ቁጥሮችን ብዙ ሰዎች በሚጠቀሙበት የመፈጊያ ገጽ በነጻ ለማየት የክሮም ዲቨሎፐር መሣሪያዎችን መጠቀም) በዩታ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር በሆኑት ሾን ላውሰን በ2019 የታተመ፣
‹Step by step guide to safely accessing the darknet and deep web, an article› በፖል ቢስቾች እና VPN & Privacy, የComparitech.com የህትመት ውጤት ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች እንደ ቪፒኤን ያሌ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን ሰብስክራይብ ሲያደርጉ፣ ያለጥርጣሬና በመተማመን እንዲወስኑ የሚረዳቸው የኢንግሊዝ ኩባንያ ነው
research-beyond-google፤ 56 እምነት የሚጣልባቸው፣ የማይታዩ እና ሁሉን አካታች ምንጮች፣ ይህም የወል ከሆነ የትምህርት ዳታ ቤዝ የሚገኝ ምንጭ ሲሆን፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ ኦንላይን ትምህርትን፣ በነጻ እንዲሁም በዱቤ የሚሰጡ ትምህርቶች የሚሰጥ በአሜሪካ የሚገኝ ተቋም፣፣
‹The Engine Room› መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ዓለማቀፍ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ለድር ምንጮች የመግቢያ ሐሳቦችን የፈጠረ ሲሆን በዚህም መረጃው እንዳይጠፋ ወይም እንዳይቀየር ግልባጭ የሚቀመጥበት ክፍልን ያጠቃልላል።
‹Awesome Public Datasets› ትልቅና በኅብረት የተሠራ በርዕሰ ጉዳይ የተደራጀ ክምችት፣
ከStart.me የሚገኙ ምንጮች፤ የተያያዙ ‹ቡክማርኮች› መምሪያ ካዘጋጁ ኩባንያዎች የሚገኙ እጅግ በርካታ ምንጮች መገኛ ነው። ከመቶ በላይ ማግኛ/ሊንኮች የሚገኙበት ነጻ ላይብረሪ ነው፤
ለምሳሌ ዳታ ቤዝ፣ ሰፊ ጉዳዮች የሚያካትት፣ ስከ ተሰረቁ ንብረቶች፣ የአየር ፀባይ፣ ሚድያ፣ ትራፊክ፣ ትንታኔዎች፣ የዶሜይን ምዝገባ፣ ሕንጻዎች፣ ስለእንስሳት፣ ገንዝብ እና ሌሎችንም በሚመለከተ ማግኛ/ሊንኮች ያሉት ነው።
‹Bates InfoTips› በሜሪ ኤለን ቤትስ የተዘጋጀ፣ የታደሱ ሐሳቦች የሚገኙበት ጥሩ ምንጭ ነው። ለምሳሌ የጎግል ዜና ፍለጋዎችን በሰዓት እንደመገደብ እና በፌስቡክ መፈለጊያ/ማሰሻ ሰዎችን መፈለግ የመሳሰሉትን ያካትታል። ቤትስ የቤትስ የመረጃ አገልግሎት መሥራችና ኃላፊ የረጅም ጊዜ የመራጃ ባለሞያ ናት።
‹ሪሰርች በዝ› የተባለ ገጽ እንደጻፈው፣ ከፍለጋ ውጤት ውስጥ የማይፈለጉ ገጾችን ለይቶ ለማስቀረት፣ የጎግል ፍለጋ ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታትም የድሮ/የቆየውን መንገድ መጠቀም፤
በመደበኛ የሚታወቁትን እንደ አራቱ ድብቅ የሆኑ የድር ማሰሻዎች ያሉ ጥሩ ጠቃሚ ነጥቦች ተጠቀም፤
እንደሚያስፈልጋችሁ ያላወቃችሁት፣ ስድስት የተለዩና ነጻ የቁልፍ ቃላት መፈለጊያ መሣሪያዎች፣ ከመፈለጊያ ኢንጅን ጥናታዊ መጽሔት።
ይህ መሣሪያ በዙሪያህ ያሉ በግልጽ የሚታዩ ካሜራዎችን ያሳያል፣ ካመርካ እንዴት አድራሻ እንደሚቀበል፣ ቦታዎችን እንዴት እንደሚያውቅ፣ በካርታ ላይ በኢንተርኔት የተሳሰሩ ካሜራዎችን የሚያሳይና የሚያስረዳ ጽሑፍ፣
‹Open-Source Intelligence (OSINT) Reconnaissance› የጥናት ባለሞያ-ጸሐፊ-ሀከር-አሳቢ የሆነው የኢያን ባርዊስ ረጅም ጽሑፍ፣ በመካከለማ መጠን እንደ ‹ጎግል ዶርኪንግ› ላሉ ዘዴዎች ሽፋን ሰጥቷል።
‹After the GDPR: researching domain name registrations› የአውሮፓን የጠቅላላ መረጃ ጥበቃ መመሪያ የፈጠረውን ተፅእኖ መመልከት፣ የመፈለጊያ ዶሜኖችን ሥም ምዝገባ ከባድ ሲያደርገው፣ የተለያዩ መሣሪያዎችንና ዘዴዎችን መጠቀም ግን ይላል፣ እንደ OSINTCurious ገለጻ።
የፌስቡክ ግራፍ መፈሊያ ጥያቄዎች እንዴት እንደሚጻፉ፤ ይህም በፌስቡክ ፖስት የተረደጉትን፣ አስተያየቶችን፣ ሰዎችን እና ሌሎች አካላትን ግራፍ የምንፈልግበት የ2020 ‹ዊኪ-ሀው› መመሪያ፤
በቤሊንግካት መርማሪና አሠልጣን የሆነችው ቻርሎት ጎዳርት የተዘጋጀ ምንአልባት አለ የተባለ ስፋት ያለው የትዊትዴክ ምርምር መመሪያ፣
የተደበቁ የንግድ ምንጮችን ማግኘት፣ በጥልቅ ድሮች ላይ የተፈለገውን ለማግኘት በኤለን ቤትስ የተሠራ፣ በ2019 የቤተመጻሕፍት ልዩ ማኅበር ኮንፈረንስ ላይ የቀረበ ገለጻ።
በጎግል ፋንታ ለረትጠቀሙ የምትችሏቸው 17 ምርጥ መፈለጊያዎች፣ በ2020 የመፈለጊያ ኢንጅኖች ጥናታዊ መጽሔት ላይ የታተመ፤
የኢንስታግራም የመገኛ ፍለጋ፤ ለተጨማሪ የፍለጋ አማራጮች የኢንስታግራም ማብራሪያን ይመልከቱ