Accessibility Settings

color options

monochrome muted color dark

reading tools

isolation ruler

ሃብት

በአፍሪካ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ፡ ፀጥታና ደኅንነት በአፍሪካ

Read this article in

በተፈጥሮው፣ የምርመራ ጋዜጠኝነት አደገኛ ሲሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ዘጋቢዎችና ኤዲሪተሮችን ስጋት ላይ ይጥላል። ሙሰኛ የሆኑና እጃቸው የዘረመ የመንግሥት ባለሥልጣናት ቆሻሻ የሚያወጡ ጋዜጠኞች ማስፈራሪያዎ ይገጥሟቸዋል። ይህም የምርመራ ሥራውን ለማስቆም የሚድያ ተቋማቸውን እስከመጨረሻው ዝም እስከማሰኘት የሚደርስ ጥረት ነው። እነዚህን ጋዜጠኞች ከደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት ለመጠበቅ፣ አንዳንድ የአፍሪካ እና ዓለማቀፍ ድርጅቶች፣ በተመረጡ የአፍሪካ አገራትም ሆነ በመላው አኅጉሪቱ፣ ችግር ላይ ላሉ ምስጢር አጋላጭ ጋዜጠኞች ድጋፍ የሚያቀርቡበትን ፕሮግራም ሠርተዋል።

የአፍሪካ ሰብአዊ መብት ኔትወርክ

የአፍሪካ ሰብአዊ መብት ኔትወርክ መጠለያ ለሆኑ እንደ ዳሬሰላም እና በቤኒን ያሉ ከተሞች፣ የሰፈራ ፕሮግራሞችን ያቀርባል። አገልግሎቱም ለምርመራ ጋዜጠኞች እና ሌሎች በአፍሪካ ስጋት ላይ ያሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ሰፈራ በሚደረግባቸው ወቅቶች የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማስቻል የቀረበ ነው። ይህ አገልግሎት የትራንስፖርት፣ ማረፊያ እና ኑሮ፣ የሕክምና እርዳታና መድኅን፣ የሳይኮሶሻል ድጋፍ፣ የአቅም ግንባታ እና ሥልጠና፣ በርቀት እያሉ ሥራን ማስቀጠል፣ የልውውጥና የኔትወርክ ፕሮግራሞች እንዲሁም ወደ አገር ቤት በደኅና መመለስና ሥራን መቀጠልን ያጠቃልላል።

የአፍሪካ የመረጃ ልውውጥ ኔትወርክ

የአፍሪካ የመረጃ ልውውጥ ኔትወርክ (AFEX) በሰብ ሰሃራ አፍሪካ 15 የሚጠጉ፣ በአካባቢያቸው የፕሬስ ነጻነትን ለማሻሻልና ለማጠናከር በቅርበት የሚሠሩ፣ የመናገር ነጻነት ተቋማት ኔትወርክ ነው። እነዚህም የዓለማቀፉ የመረጃ ልውውጥ ኔትወርክ (IFEX) አባላት ናቸው።

ኔትወርኩ በአፍሪካ የመናገር ነጻነትን እና ሰብአዊ መብትን ያስተዋውቃል። ይህንንም የሚያደርገው በቅስቀሳና ዘመቻ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ሲሆን፣ በዚህም የአባላቱንና በክልሉ ሌሎች የመናገር ነጻነት ላይ የሚሠሩ ቡድኖችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ነው። የኔትወርኩ ጽሕፈት ቤት መቀመጫውን በጋና ያደረገው የምዕራብ አፍሪካ ሚድያ ፋውንዴሽን ነው።

አርቲክል 19

መቀመጫውን ኢንግሊዝ ያደረገው ‹አርቲክል 19›፣ በዓለም ዙሪያ የመናገርና መረጃ የማግኘት ነጻነትን ለማጠናከር በዓለም ዙሪያ የሚሠራ ነው። እንቅስቃሴዎቹም የሕግ ስርዓቶችን ማውጣት፣ የሕግ ትንታኔዎችን መስጠት፣ የብሔራዊ ሕጎችን መተቸት፣ በዓለማቀፍና አገራዊ ፍርድ ቤቶች፣ መብታቸው በተጣሰ በግለሰቦችና ቡድኖች ስም መሟገትን ያጠቃልላል። ‹አርቲክል 19› ከሌሎች የሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች ጋር በትብብር ይሠራል። በሰብ ሰሃራ አፍሪካ፣ በሴኔጋል እና ኬንያ የክልል ቢሮዎች አሉት። በምዕራብና ምሥራቅ አፍሪካም ኹለት የክልል ፕሮግራሞችን ያካሂዳል።

በደቡብ ሱዳን የሚድያ ልማት ማኅበር

ደቡብ ሱዳን ከሰብ ሰሃራ አፍሪካ አገራት ጋዜጠኝነትን ለመለማመድ አደገኛ ከሆኑ ቦታዎች መካከል ናት። ይህ የሆነው የትኛውም ዓይነት ወሳኝ የሆነ ዘገባ ቢሠራ፣ ጋዜጠኞችን ጸረ ሰላምና የአሸባሪዎቸ ተባባሪ በማለት ወታደራዊው መንግሥት ስለሚጨፈልቃቸው ነው። በዚህ ከባድ አካባቢ፣ በደቡብ አፍሪካ የሚድያ ልማት ማኅበር፣ በአገሪቱ የፕሬስ ነጻነት እንዲኖር ከሚቀሰቅሱ ተቋማት መካከል አንዱ ነው። ለዚህም ከሌሎች የአገር ውስጥ ድርጅቶችና ዓለማቀፍ አጋሮች ጋር በጋራ ይሠራል። በ2015 የሚድያ ልማት ተቋም የመሠረተ ሲሆን፣ ይህም በሥራ ላይ ላሉና ለሚፈልጉ ጋዜጠኞች፣ በጋዜጠኝነት የዘጠኝ ወራት የሰርተፍኬት ፕሮግራም የሚያቀርብ ነው።

በአፍሪካ ጋዜጠኞችን ጠባቂ ኮሚቴ (CPJ Africa)

ይህ ጋዜጠኞችን ጠባቂ ኮሚቴ (CPJ)፣ ራሱን የቻለ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሲሆን፣ ኃላፊነቱም ጋዜጠኞች ዘገባዎችን በደኅንነት እና ያለምንም ዓይነት ፍርሃት የመዘገብ መብታቸውን መከላከል ነው። የአፍሪካው ኮሚቴ ከዚህ በተጨማሪ የደኅንነት ጉዳዮችን በመሰነድ፣ የደኅንነት ምክሮችን እና መሣሪያዎች  በአደጋ ጊዜ ለጋዜጠኞች መስጠት እንዲሁም ድንገተኛ ጊዜ ምላሽ መስጠት አገልግሎትን ይሰጣል።

ፍሪ ፕሬስ አንሊሚትድ› (ያልተገደበ ነጻ ፕሬስ)

ኹለት ፕሮግራሞች ያሉት ሲሆን፣ እነዚህም ለሚድያ ባለሞያዎች፣ ጋዜጠኞችና ተቋማት በዓለማቀፍ ደረጃ የድንገተኛ ጊዜ ትብብሮችን ለመስጠት ያለመ ነው።  ለዘጋቢዎች የድንገተኛ ጊዜ የድጋፍ ምላሽ፣ ለጋዜጠኞች እና ለሚድያ ማሰራጫዎች፣ ችግር በሚያጋጥም ጊዜ ሥራቸውን በተቻለ ፍጥነት እንዲቀጥሉ ለማስቻል በቀጥታ የሚደረግ ድጋፍ ነው። በሕግ መከላከያ ድጋፍ ደግሞ ለሚድያ ባለሞያዎችን በሕግ ጉዳዮች ዙሪያ ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህም ለምሳሌ ጋዜጠኞች ወይም ቤተሰቦቻቸው ክስ እና እስር ሲገጥማቸው እና የጠበቃና የፍርድ ወጪዎችን መክፈል ሳይችሉ ሲቀሩ የሚደረግ ነው።

በዩጋንዳ ለጋዜጠኞች የሰብአዊ መብት ኔትወርክ

በ2005 የተመሠረተው በዩጋንዳ ለጋዜጠኞች የሰብአዊ መብት ኔትወርክ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ የሕገ መንግሥት መብቶቻቸውና መሠረታዊ ነጻነቶቻው ለተጣሱባቸው ዘጋቢዎችን ለማገዝ የሚሠሩ፣ ጡረታ የወጡ እንዲሁም በሥራ ላይ ያሉ ጋዜጠኞች በጋራ የሚገኙበት ነው። ተቋሙ ጥናታዊ ሥራዎችን ያከናውናል፣ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ማስፈራሪያና ጥቃቶችን እንዲሁም በዩጋንዳ የፕሬስ ነጻነትን ይከታተላሉ፣ ይሰንዳሉ። በተጨማሪም ሥራቸው የሕግ እርዳት እንዲያስፈልጋቸው ግድ ላለ ጋዜጠኞች የሕግ ድጋፍ ያደርጋሉ።

ዓለማቀፍ የሚድያ እገዛ (IMS)

ይህ ተቋም የጋዜጠኞችን መብት የሚከላከል ነው። በተጨማሪም ጋዜጠኞች ሥራቸውን በመሥራታቸው በሚጠቁባቸውና በሚንገላቱባቸው እንዲሁም ግጭቶች ከፍተኛ ደረጃ ደርሰው ዘገባ ለመሥራት አደገኛ በሚሆንባቸው አገራት ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሠሩ ለማረጋገጥ ነው። በደኅንነት ድጋፉም፣ በቀጥታ በጋዜጠኝነት ሥራቸው ጥቃት ለደረሰባቸው ጋዜጠኞች ፈጣን እርዳታ ይሰጣል።

የሚድያ መከላከያ

የሚድያ የሕግ መከላከያ ኢኒሺዬቲቭ (በቅርቡ ሥያሜውን ወደ ሚድያ መከላከያ የሚቀይር)፣ የድንገተኛ ጊዜ ድጋፍን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ ይህም ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች እና ራሳቸውን የቻሉ ሚድያዎች የሕግ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ እንዲሁም እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ላይ ለሚሠሩ የሕግ ባለሞያዎች የሕግ ሞያዊ ድጋፍ በማቅረብ የሚረዳ ነው። ይህን ድጋፍ ለማግኘት የሚሹ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮችና የሕግ ባለሞያዎችም እዚህ ጋር ማመልከት ይችላሉ። መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ይህ ተቋም፣ የዲጂታል መብቶች አቀንቃኝ ፕሮጀክቱ አንድ አካል አድርጎ፣ በምሥራቅ፣ ምዕራብ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ የሕግ ባለሞያዎች ትስስር/ኔትወርክ እየገነባ ነው።

የሕግ ባለሞያዎች በኦንላይን ራስን የመግለጽ ነጻነት ጉዳዮች ላይ የሚሠሩ ሲሆን፣ ጉዳዮቹም በጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች እና የሚድያ ማሰራጫዎችን የተመለከተ ነው። ሚድያ መከላከያ በአፍሪካ የዲጂታል መብት እና የመናገር ነጻነትን በሚመለከት፣ በአፍሪካ ዙሪያ በርካታ የሚባሉ የምንጭ ግብዓቶች አሉት።

የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ኤዲተሮች ፎረም (SANEF)

የዚህ የደቡብ አፍሪካ ተቋም አባላት ኤዲተሮችመ ከፍተኛ ጋዜጠኞች፣ የሚድያ አመራሮች እና ከፍተኛ የጋዜጠኝነት አሠልጣኖች ናቸው። የተቋሙ ዋና ግብ እተወካይ እና በደቡብ አፍሪካ ተዓማኒ የጋዜጠኞች ድምጽ መሆን ነው። በተጨማሪም የአገሪቱን በብዙ ትግል የተገኙ የሚድያና የመንገር ነጻነቶችን ለመጠበቅ አልሟል። በአገሪቱም ለሚኖሩ የፕሬስ ነጻነት ጉዳዮች ዙሪያ ተከታታይና ተደማጭ ተናጋሪም ነው። መግለጫዎቹም እንደ ዘርፉ ጥቅል ሐሳብ ይቆጠራሉ።

ፎረሙ የሚድያ ነጻነትን ከሚጋፋና ሊያግዱ ከሚሞክሩ ማስፈራሪያዎች በተቃራኒ ሆኖ ቅስቀሳ ያደርጋል፣ የሥልጠና ኢኒሺዬቲቮችን ያቀርባል፣ የማኅበረሰብ ሚድያ ጉዳዮችን ያገዝፋል እንዲሁም ከሌሎች የሚድያ ልማት እና የንግግር ነጻነት ላይ ከሚሠሩ ተቋማት ጋር ይተባበራል። አባልነት በጥቆማ የሚገኝ ሲሆን፣ ዓመታዊ ክፍያንም ይጠይቃል።  በደቡብ አፍሪካ የሚድያ ነጻነት ዙሪያ የተሠሩ ጥናታዊ ሥራዎችን እና የፖሊሲ ሰነዶች ዝርዝር ያስቀምጣል

የታንዛንያ የሰብአዊ መብት ተከላካዮች ጥምረት (THRDC)

ይህ ጥምረት በ2010 የተመሠረተ ሲሆን የምሥራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብት ጠባቂዎችን ደኅንነትና ጥበቃ ላማጠናከር የተቋቋመ ነው። ጥምረቱ በታንዛንያ ደኅንነት፣ ክብርና የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተሟጋቾችን ጥረት ጥበቃ በመስጠት፣ አቅም በማሳደግና በቅስቀሳ የሚደግፍ ነው።

የቶተም ፕሮጀክት

በ‹ግሪንሆስት› እና ‹ፍሪ ፕሬስ ሊሚትድ› ትብብር የተመሠረተው ቶተም፣ የኦንላይን መማሪያ አውድ ሲሆን፣ ስለዲጂታል ደኅንነት እና ምስጢራዊነት እንዲሁም ተያያዝ የሆኑ መሣሪያና ሥልቶችን ለጋዜጠኞች፣አ አክቲቪስቶች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ደኅንነት በተጠበቀ መልኩ የኦንላይን ትምህርቶችን የሚሰጥ ነው። ይህ አውድ Open edX MOOC (ሰፊ ግልጽ የኦንላይን ትምህርት) በተባለ የወል የሆነ መረጃ ምንጭ ሶፍትዌር የተሠራ ነው። ይህ አውድ የተጠቃሚዎቹን ውስን መረጃ በመሰብሰብ እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት ስለላ ለመቋቋም የሚችሉ፣ ደኅንነታቸው የተጠበቀና ዘመናዊ ኢንክሪፕሽኖችን በመጠቀም ደኅንነቱ የተጠበቀና ምሥጢር የሚጠብቅ እንዲሆን ተደርጎ ተቀርጿል።

የዚምባቡዌ የበጎ ፈቃደኞች የሚድያ ምክር ቤት (VMCZ)

በዚምባቡዌ የሚድያ ነጻነት ዙሪያ የሚሠራ የጋዜጠኞች፣ አሳታሚዎች፣ የሚድያ ቤቶች እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች ኅብረት ነው። የተመሠረተው በ2007 ሲሆን፣ በአገሪቱ ሚድያ ራሱን እንደቻለ አንድ ተቆጣጣሪ አካል የሚንቀሳቀስ ነው። በመገናኛ ብዙኀን ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች ይዳኛል፣ ጣልቃም ይገባል። እንዲሁም በሚድያ፣ በመንግሥትና በፖለቲካው ተዋንያን መካከል እንደ አገናኝ ያገለግላል።

ጋዜጠኞችን በተወሰነ መንገድ ለማገዝ ያስችለው ዘንድ አቅምን ለማዳበር የሚያስችሉ ሙያዊ ሥልጠናዎችን ያቀርባል። ከእነዚህ ሥልጠናዎች አብዛኞቹ ትኩረታቸው በምርመራ ጋዜጠኝነት ብቃቶች ላይ ነው። ምክር ቤቱ በዚምባቡዌ ‹የሚድያ እና የምርመራ ጋዜጠኝነት› የተባለውን ትልቁን የሚድያ ሽልማት ያዘጋጃል።

በፀጥታና ደኅንነት ዙሪያ ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት፣ ወደ ኔትወርኩ የእርዳታ ዴስክ ይሂዱ፤

Republish our articles for free, online or in print, under a Creative Commons license.

Republish this article


Material from GIJN’s website is generally available for republication under a Creative Commons Attribution-NonCommercial 4.0 International license. Images usually are published under a different license, so we advise you to use alternatives or contact us regarding permission. Here are our full terms for republication. You must credit the author, link to the original story, and name GIJN as the first publisher. For any queries or to send us a courtesy republication note, write to hello@gijn.org.

Read Next

የናይጄሪያው ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) በኮቪድ 19 ምላሽ ተጠሪነትን ለመፍጠር እያደረገ ያለው ግፊት

መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።